ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “ከእናንተ ጋር ያሉ እንግዶች አማልክትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ ልብሳችሁንም እጠቡ፤
መዝሙር 116:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ሁላችሁ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፥ ወገኖችም ሁሉ ያመስግኑት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃሌ ሉያ! ጌታ የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ። |
ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “ከእናንተ ጋር ያሉ እንግዶች አማልክትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ ልብሳችሁንም እጠቡ፤
እግዚአብሔርም አለው፥ “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ እንደ ጸሎትህም ሁሉ አደረግሁልህ፤ ለዘለዓለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖችና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ።
ዐይኖች ደከሙ፤ ወደ ሰማይም ወደ እግዚአብሔር ማየት አልቻልሁም። ጌታ ሆይ፦ ይቅር በለኝ፤ የሰውነቴንም መከራ አርቅልኝ።
“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ የጩኸቴን ድምፅ ሰማኝ፤ ቃሌንም አዳመጥህ።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፤ ከነዓናውያንንም አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ እነርሱንም፥ ከተሞቻቸውንም ሕርም ብለው አጠፉአቸው፤ የዚያን ስፍራ ስም “ሕርም” ብለው ጠሩት።
በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኀይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው፡” አለው።
ሦስተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ ጴጥሮስም ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ስላለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “እንኪያስ ግልገሎችን ጠብቅ” አለው።
እርስዋም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ በዚህ በፊትህ ቆማ የነበረች ሴት እኔ ነኝ።