Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 116 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሃሌ ሉያ! ጌታ የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት።

2 ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።

3 የሞት ገመዶች ወጠሩኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፥ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።

4 የጌታን ስም ጠራሁ፦ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።

5 ጌታ መሓሪና ጻድቅ ነው፥ አምላካችንም ርኅሩኅ ነው።

6 ጌታ የዋሆችን ይጠብቃል፥ ተዋረድሁ፥ እርሱም አዳነኝ።

7 ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ ጌታ መልካም አድርጎልሻልና፥

8 በእርግጥም ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥ እግሬንም ከመሰናከል አድነሃል።

9 በሕያዋን አገር በጌታ ፊት እሄዳለሁ።

10 አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ፥ እኔም እጅግ ተቸገርሁ።

11 እኔም ከድንጋጤዬ የተነሣ፦ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው አልሁ”።

12 ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለጌታ ምንን እመልሳለሁ?

13 የመድኃኒትን ጽዋ ከፍ አደርጋለሁ፥ የጌታንም ስም እጠራለሁ።

14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፥ እነሆ ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ።

15 የቅዱሳኑ ሞት በጌታ ፊት የከበረ ነው።

16 አቤቱ፥ እኔ አገልጋይህ ነኝ፥ አገልጋይህ፥ የሴት አገልጋይህም ልጅ ነኝ፤ ሰንሰለቴን ሰበርህ።

17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕትን እሠዋለሁ፥ የጌታንም ስም እጠራለሁ።

18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ፥

19 በጌታ ቤት አደባባይ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በመካከልሽም እንዲሁ። ሃሌ ሉያ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos