መዝሙር 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፉ በመርገም፥ በሽንገላና በዐመፃ የተመላ ነው፥ ከምላሱ በታች ተንኰልና ክፋት አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግሩም በእርግማን፥ በሐሰትና በዛቻ የተሞላ ነው፤ ተንኰልና ክፉ ነገር በአንደበቱ ናቸው። |
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
የጽድቁን መሥዋዕት፥ መባውንም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያንጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።
ጽድቅን የሚናገር በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በከንቱ ነገር ታምነዋል፤ የማይጠቅማቸውንም ተናግረዋል፤ ኀጢአትን ፀንሰዋል፤ በደልንም ወልደዋል።
“ምላሳቸውን ለሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥” ይላል እግዚአብሔር።
አራጣንም በአራጣ ላይ ይቀበላሉ፤ ተንኰልን በተንኰል ላይ ይሠራሉ፤ “እኔንም ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።