ፊልጵስዩስ 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛስ ሀገራችን በሰማይ ያለችው ናት፤ ከዚያም እርሱን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ግን አገራችን በሰማይ ነው፤ ከዚያ የሚመጣውንም አዳኝ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በናፍቆት እንጠባበቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፤ ከዚያም የሚመጣውን አዳኝ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ግን የሰማይ መንግሥት ዜጎች ነን፤ ከዚያም የሚመጣውን አዳኝ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በናፍቆት እንጠባበቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ |
አቤቱ፥ ከተግሣጽህ፥ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።
እነርሱም፥ “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየአያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ፥ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” አሏቸው።
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ተስፋ አናደርግም፤ የሚታየው ኀላፊ ነውና፥ የማይታየው ግን ለዘለዓለም የሚኖር ነው።
እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።
የሚሻለውን ሥራ እንድትመረምሩና እንድትፈትኑ፥ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ያለ ዕንቅፋት ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ፦
ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን።
የእውነት ቃል በሆነው በወንጌል ትምህርት፥ አስቀድሞ ስለ ሰማችሁት፥ በሰማይ ስለ ተዘጋጀላችሁ ተስፋችሁም እንጸልያለን።
ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።
እናንተ ግን፥ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደምትሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰማያት ወደ አለችው ኢየሩሳሌም፥ ደስ ብሎአቸው ወደሚኖሩ አእላፍ መላእክትም ደርሳችኋል።
እንዲሁ ክርስቶስም የብዙዎችን ኀጢአት ያስተሰርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድናቸው ዘንድ ተስፋ ለሚያደርጉት ያለ ኀጢአት ይገለጥላቸዋል።