Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ሉቃስ 12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ስለ ፈሪ​ሳ​ው​ያን እርሾ

1 በዚ​ያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው እስ​ኪ​ረ​ጋ​ገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን እርሾ ተጠ​በቁ፤ ይኸ​ውም ግብ​ዝ​ነት ነው።

2 የማ​ይ​ገ​ለጥ የተ​ሰ​ወረ፥ የማ​ይ​ታ​ይም የተ​ሸ​ሸገ የለ​ምና።

3 በጨ​ለማ የም​ት​ና​ገ​ሩት በብ​ር​ሃን ይሰ​ማል፤ በእ​ል​ፍ​ኝም ውስጥ በጆሮ የም​ት​ን​ሾ​ካ​ሾ​ኩት በሰ​ገ​ነት ይሰ​በ​ካል።

4 ለእ​ና​ንተ ለወ​ዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሥጋ​ች​ሁን የሚ​ገ​ድ​ሉ​ትን አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ከዚ​ህም የበ​ለጠ ማድ​ረግ የሚ​ች​ሉት የላ​ቸ​ውም።

5 ነገር ግን፤ የም​ት​ፈ​ሩ​ትን አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተስ ከገ​ደለ በኋላ ወደ ገሃ​ነም ሊጥል ሥል​ጣን ያለ​ውን ፍሩት፤ አዎ፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እር​ሱን ፍሩ።

6 አም​ስት ወፎች በሁ​ለት ሻሚ መሐ​ለቅ ይሸጡ የለ​ምን? ከእ​ነ​ርሱ አን​ዲቱ ስን​ኳን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አት​ረ​ሳም።

7 የእ​ና​ን​ተስ የራስ ጠጕ​ራ​ችሁ ሁሉ የተ​ቈ​ጠረ ነው፤ እን​ግ​ዲህ አት​ፍሩ፤ ከብዙ ወፎች እና​ንተ ትበ​ል​ጣ​ላ​ች​ሁና።

8 “እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ በሰው ፊት የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝን ሁሉ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት አም​ነ​ዋ​ለሁ።

9 በሰው ፊት የሚ​ክ​ደ​ኝን ግን እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት እክ​ደ​ዋ​ለሁ።

10 በሰው ልጅ ላይ የስ​ድብ ቃል የሚ​ና​ገር ሁሉ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ላይ የስ​ድብ ቃል የሚ​ና​ገር ግን በዚህ ዓለ​ምም ሆነ በሚ​መ​ጣው ዓለም አይ​ሰ​ረ​ይ​ለ​ትም።

11 ወደ አደ​ባ​ባይ ወደ ሹሞ​ቹና ወደ ነገ​ሥ​ታቱ፥ ወደ መኳ​ን​ን​ቱም በሚ​ወ​ስ​ዱ​አ​ችሁ ጊዜ የም​ት​ሉ​ት​ንና የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን አታ​ስቡ።

12 ያን​ጊዜ በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ና​ገ​ረው መን​ፈስ ቅዱስ ነውና።”


ርስት ሊካ​ፈል ስለ ወደ​ደው ሰው

13 ከሕ​ዝ​ቡም አንዱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ርስ​ቴን እን​ዲ​ያ​ካ​ፍ​ለኝ ለወ​ን​ድሜ ንገ​ረው” አለው።

14 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንተ ሰው፥ በእ​ና​ንተ ላይ አካ​ፋ​ይና ዳኛ አድ​ርጎ ማን ሾመኝ?” አለው።

15 “ዕወቁ፤ ከቅ​ሚ​ያም ሁሉ ተጠ​በቁ፤ ሰው የሚ​ድን ገን​ዘብ በማ​ብ​ዛት አይ​ደ​ለ​ምና” አላ​ቸው።


እር​ሻው ስለ በጀ​ለት ባለ​ጸጋ

16 ምሳ​ሌም መሰ​ለ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፤ “እር​ሻው የበ​ጀ​ለ​ትና ሀገር የተ​መ​ቸው አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ።

17 እህ​ሌን የማ​ኖ​ር​በት የለ​ኝ​ምና ምን ላድ​ርግ ብሎ በልቡ ዐሰበ።

18 እር​ሱም አለ፦ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጎተ​ራ​ዬን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ጎተ​ራም እሠ​ራ​ለሁ፤ እህ​ሌ​ንና በረ​ከ​ቴ​ንም በዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ።

19 ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዲህ እላ​ታ​ለሁ፦ ሰው​ነቴ ሆይ፥ የሰ​በ​ሰ​ብ​ሁ​ልሽ ለብዙ ዓመ​ታት የሚ​በ​ቃሽ የደ​ለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበ​ልሽ።

20 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍ​ስ​ህን ከሥ​ጋህ ለይ​ተው ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ ያጠ​ራ​ቀ​ም​ኸው ለማን ይሆ​ናል? አለው።

21 ሀብ​ትን ለራሱ የሚ​ሰ​በ​ስብ፤ ሀብ​ቱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ሆነ እን​ዲሁ ነው።”


በከ​ንቱ መጨ​ነቅ ስለ​ማ​ይ​ገባ

22 ለደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ህ​ዋ​ለሁ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ስለ​ም​ት​በ​ሉ​ትና ስለ​ም​ት​ጠ​ጡት፥ ለሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁም ስለ​ም​ት​ለ​ብ​ሱት አት​ጨ​ነቁ።

23 ነፍስ ከም​ግብ ትበ​ል​ጣ​ለ​ችና፤ ሰው​ነ​ትም ከል​ብስ ይበ​ል​ጣ​ልና።

24 የማ​ይ​ዘ​ሩ​ት​ንና የማ​ያ​ጭ​ዱ​ትን፥ ጎተ​ራና ጕድ​ጓድ የሌ​ላ​ቸ​ውን የቍ​ራ​ዎ​ችን ጫጭ​ቶች ተመ​ል​ከቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ይመ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ከወ​ፎች እን​ዴት እጅግ አት​በ​ል​ጡም?

25 ከእ​ና​ን​ተስ ዐስቦ በቁ​መቱ ላይ አንድ ክንድ መጨ​መር የሚ​ቻ​ለው ማነው?

26 ይህን ቀላ​ሉን የማ​ት​ችሉ ከሆነ በሌ​ላው ለምን ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ?

27 እነሆ፥ አበ​ባ​ዎ​ችን እን​ደ​ሚ​ያ​ድጉ ተመ​ል​ከቱ፤ አይ​ፈ​ት​ሉም፤ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ነገር ግን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሰሎ​ሞን እንኳ በክ​ብሩ ዘመን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ አል​ለ​በ​ሰም።

28 እነሆ፥ ዛሬ ያለ​ውን፥ ነገም ወደ እሳት የሚ​ጣ​ለ​ውን የአ​በባ አገዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ከሆነ፥ እና​ንተ እም​ነት የጐ​ደ​ላ​ችሁ፥ ለእ​ና​ን​ተማ እን​ዴት አብ​ልጦ አያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ?

29 እና​ን​ተም የም​ት​በ​ሉ​ት​ንና የም​ት​ጠ​ጡ​ትን አት​ፈ​ልጉ፤ ወዲ​ያና ወዲ​ህም አት​በሉ፤ አት​ጨ​ነ​ቁ​ለ​ትም።

30 ይህን ሁሉ በውጭ ያሉ የዓ​ለም አሕ​ዛብ ይሹ​ታ​ልና፤ ለእ​ና​ን​ተስ አባ​ታ​ችሁ ይህን ሁሉ እን​ደ​ም​ት​ሹት ያው​ቃል።

31 ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥ​ትና ጽድቅ ሹ፤ ይህም ሁሉ ይጨ​መ​ር​ላ​ች​ኋል።

32 “አንተ ታናሽ መንጋ፥ አት​ፍራ፤ አባ​ታ​ችሁ መን​ግ​ሥ​ቱን ሊሰ​ጣ​ችሁ ወዶ​አ​ልና።

33 ሀብ​ታ​ች​ሁን ሸጣ​ችሁ ምጽ​ዋት ስጡ፤ ሌባ በማ​ያ​ገ​ኝ​በት ነቀ​ዝም በማ​ያ​በ​ላ​ሽ​በት፥ የማ​ያ​ረጅ ከረ​ጢት፥ የማ​ያ​ል​ቅም መዝ​ገብ በሰ​ማ​ያት ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ።

34 መዝ​ገ​ባ​ችሁ ካለ​በት ልባ​ችሁ በዚያ ይኖ​ራ​ልና።


ስለ መት​ጋት

35 “ወገ​ባ​ችሁ የታ​ጠቀ መብ​ራ​ታ​ች​ሁም የበራ ይሁን።

36 እና​ን​ተም፥ በመ​ጣና በር በመታ ጊዜ ወዲ​ያው ይከ​ፍ​ቱ​ለት ዘንድ ከሰ​ርግ እስ​ኪ​መ​ለስ ጌታ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ሰዎች ሁኑ።

37 ጌታ​ቸው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ር​ጉና ሲተጉ የሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው፤ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወገ​ቡን ታጥቆ በማ​ዕድ ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፤ እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸ​ዋል።

38 ከሌ​ሊቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወይም በሦ​ስ​ተ​ኛው ክፍል ቢመ​ጣና እን​ዲሁ ቢያ​ገ​ኛ​ቸው እነ​ዚያ አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው።

39 ነገር ግን ይህን ዕወቁ፤ ባለ​ቤት ሌባ የሚ​መ​ጣ​በ​ትን ጊዜ ቢያ​ውቅ ተግቶ በጠ​በቀ፥ ቤቱ​ንም እን​ዲ​ቈ​ፍ​ሩት ባል​ፈ​ቀ​ደም ነበር።

40 እና​ን​ተም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ ባል​ጠ​ረ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ሰዓት ይመ​ጣ​ልና።”

41 ጴጥ​ሮ​ስም፥ “አቤቱ፥ ይህን ምሳሌ የም​ት​ና​ገ​ረው ለእኛ ነውን? ወይስ ለሁሉ ነው?” አለው።

42 ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታው በቤ​ተ​ሰቡ ላይ የሚ​ሾ​መው ደግ ታማ​ኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?

43 ጌታው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ርግ የሚ​ያ​ገ​ኘው አገ​ል​ጋይ ብፁዕ ነው።

44 እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ በሀ​ብቱ ሁሉ ላይ ይሾ​መ​ዋል፤

45 ነገር ግን ያ ክፉ አገ​ል​ጋይ በልቡ፦ ጌታዬ ቶሎ አይ​መ​ጣም ቢል፥ በጌ​ታው ቤት ያሉ​ት​ንም ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮች ሊደ​በ​ድ​ብና ሊያ​ጕ​ላላ ቢጀ​ምር፥ ከሰ​ካ​ራ​ሞ​ችም ጋር ቢበ​ላና ቢጠጣ፥ ቢሰ​ክ​ርም፥

46 የዚያ አገ​ል​ጋይ ጌታ ባል​ጠ​ረ​ጠ​ረው ዕለት፥ ባላ​ወ​ቀ​ውም ሰዓት መጥቶ ከሁ​ለት ይሰ​ነ​ጥ​ቀ​ዋል፤ ዕድ​ሉ​ንም ከማ​ይ​ታ​መኑ ጋር ያደ​ር​ገ​ዋል።

47 የጌ​ታ​ውን ፈቃድ ዐውቆ እንደ ፈቃዱ የማ​ይ​ሠ​ራና የማ​ያ​ዘ​ጋጅ የዚያ አገ​ል​ጋይ ቅጣቱ ብዙ ነው።

48 ያላ​ወቀ ግን ባይ​ሠ​ራም ቅጣቱ ጥቂት ነው፤ ብዙ ከሰ​ጡት ብዙ ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና። ጥቂት ከሰ​ጡ​ትም ጥቂት ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና።


ስለ ሰይ​ፍና ስለ መለ​ያ​የት

49 “በም​ድር ላይ እሳ​ትን አም​ጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ን​ደድ በቀር ምን እሻ​ለሁ?

50 ነገር ግን፤ የም​ጠ​መ​ቃት ጥም​ቀት አለ​ችኝ፤ እስ​ክ​ፈ​ጽ​ማ​ትም ድረስ እጅግ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።”

51 ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለም​ድር ሰላ​ምን ያመ​ጣሁ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን? እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አይ​ደ​ለም፤ ሰይ​ፍ​ንና መለ​ያ​የ​ትን ነው እንጂ።

52 ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ አም​ስት ሰዎች በአ​ንድ ቤት ቢኖሩ ሦስቱ ከሁ​ለቱ፥ ሁለ​ቱም ከሦ​ስቱ ይለ​ያሉ፤

53 አባት ከልጁ፥ ልጅም ከአ​ባቱ ይለ​ያል፤ እናት ከል​ጅዋ፥ ልጅም ከእ​ናቷ ትለ​ያ​ለች፤ አማት ከም​ራቷ፥ ምራ​ትም ከአ​ማቷ ትለ​ያ​ለች።”

54 ከዚ​ህም በኋላ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ደመና በም​ዕ​ራብ በኩል ደምኖ ባያ​ችሁ ጊዜ ‘ዝናም ይመ​ጣል’ ትላ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ይሆ​ናል።

55 የአ​ዜብ ነፋስ በነ​ፈሰ ጊዜም ‘ድርቅ ይሆ​ናል፤’ ትላ​ላ​ችሁ እን​ዲ​ሁም ይሆ​ናል።

56 እና​ንት ግብ​ዞች! የሰ​ማ​ዩ​ንና የም​ድ​ሩን ፊት መመ​ር​መር ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን እነ​ዚ​ህን ዘመ​ናት መመ​ር​መ​ርን እን​ዴት አታ​ው​ቁም?

57 እና​ንተ ራሳ​ችሁ እው​ነ​ቱን ለምን አት​ፈ​ር​ዱም?

58 ከባ​ለ​ጋ​ራህ ጋር ወደ ሹም በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ ወደ ዳኛ እን​ዳ​ይ​ወ​ስ​ድህ በመ​ን​ገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳ​ህ​ንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎ​ሌው አሳ​ልፎ ይሰ​ጥ​ሃ​ልና። ሎሌ​ውም በወ​ኅኒ ቤት ያስ​ር​ሃል።

59 ያለ​ብ​ህን የመ​ጨ​ረ​ሻ​ዋን ግማሽ ሣን​ቲም ቢሆን እስ​ክ​ት​ጨ​ርስ ድረስ አት​ወ​ጣም እል​ሃ​ለሁ።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos