እግዚአብሔርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግዚአብሔርም በዚያው ቀሠፈው። በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት በዚያው ሞተ።
ዘኍል 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንንና ልጆቹን በምስክሩ ድንኳን ፊት አቁማቸው፤ ክህነታቸውንም፥ በመሠዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ያለውንም ሁሉ ይጠብቁ፤ ከሌላ ወገን የዳሰሰ ቢኖር ይገደል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፤ እነርሱም ክህነታቸውን ይጠብቁ፤ ሌላ ሰው ማደሪያውን ቢቀርብ ግን ይገደል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ፤ ማናቸውም ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክህነቱንም ሥራ ያከናውኑ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፤ ከእነርሱ በቀር ሌላ ሰው ይህን ሥራ ለማከናወን ቢሞክር በሞት ይቀጣ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንንና ልጆቹን አቁማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ፤ ሌላ ሰውም ቢቀርብ ይገደል። |
እግዚአብሔርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግዚአብሔርም በዚያው ቀሠፈው። በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት በዚያው ሞተ።
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በምስክሩ ድንኳን ማደሪያ ፊት በበገና እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ለአገልግሎታቸው ይቆሙ ነበር።
በመታጠቂያም ታስታጥቃቸዋለህ፤ ቆብንም ታደርግላቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዐትም ክህነት ይሆንላቸዋል፤ እንዲሁም የአሮንንና የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ።
ድንኳንዋም ስትነሣ ሌዋውያን ይንቀሉአት፤ ድንኳንዋም ስታርፍ ሌዋውያን ይትከሉአት፤ ሌላ ሰው ግን ለመንካት ቢቀርብ ይገደል።
አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቦአል፤ ካህናትም ትሆኑ ዘንድ ትፈልጋላችሁን?
እንደ ቆሬና ከእርሱም ጋር እንደ ተቃወሙት ሰዎች እንዳይሆን፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እንዳይቀርብ፥ እግዚአብሔር በሙሴ ቃል እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።
እነርሱም ትእዛዝህን የድንኳኑንም ሕግ ይጠብቁ፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ፥ እናንተም ደግሞ ከእነርሱ ጋር እንዳትሞቱ፥ እነርሱ ወደ መቅደሱ ዕቃና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ።
አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ እንደ መሠዊያውና፥ በመጋረጃውም ውስጥ እንዳለው ሥርዐት ሁሉ ክህነታችሁን ጠብቁ፤ የሀብተ ክህነት አገልግሎታችሁንም አድርጉ፤ ከሌላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
በምሥራቅ በኩል በምስክሩ ድንኳን ፊት የሚሰፍሩት ሙሴና አሮን ልጆቹም ይሆናሉ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ሕግም የመቅደሱን ሕግ ይጠብቃሉ፥ ከሌላ ወገን የዳሰሰ ቢኖር ይገደል።
እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።
እርሱ ከልጆቹ ጋር በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ቁሞ ለዘለዓለም ያገለግል ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ መርጦታልና።
የኢያኮንዩ ልጆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመልክተው ከቤትሳሚስ ሰዎች ጋር አልተቀበሉአትም፤ እግዚአብሔርም ከሕዝቡ አምስት ሺህ ሰባ ሰዎችን መታ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለቀሱ።