Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 6:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እስ​ኪ​ሠራ ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማደ​ሪያ ፊት በበ​ገና እያ​ዜሙ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በየ​ተ​ራ​ቸ​ውም ለአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ይቆሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው፣ ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 እነርሱም ሰሎሞን የጌታን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ንጉሥ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ከመሥራቱ በፊት እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን የመዘመር ተግባራቸውን ያከናውኑ ነበር፤ የሥራቸውንም ቅደም ተከተል በተዘጋጀላቸው ተራ መሠረት ይፈጽሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 6:32
20 Referencias Cruzadas  

ዮሐ​ና​ንም ዓዛ​ር​ያ​ስን ወለደ፤ እር​ሱም ሰሎ​ሞን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሠ​ራው ቤት ካህን ነበረ፤


ዳዊ​ትም ታቦቷ በም​ታ​ር​ፍ​በት ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቆ​ማ​ቸው የመ​ዘ​ም​ራን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹና ልጆቹ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ከቀ​ዓት ልጆች ዘማ​ሪው ኤማን ነበረ፤ እር​ሱም የኢ​ዩ​ኤል ልጅ፥ የሳ​ሙ​ኤል ልጅ፤


ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች የነ​በሩ መዘ​ም​ራን በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና ሹሞች ነበሩ፤ ሥራ​ቸ​ውም ሌሊ​ትና ቀን ነበረ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የካ​ህ​ና​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ሰሞን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸ​ውና በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ በሮች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡና ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑም፥ ያከ​ብ​ሩም ዘንድ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን መደበ።


የአ​ሳ​ፍም ልጆች መዘ​ም​ራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳ​ፍም፥ እንደ ኤማ​ንም የን​ጉ​ሡም ባለ ራእይ እንደ ነበ​ረው እንደ ኤዶ​ትም ትእ​ዛዝ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ነበሩ፤ በረ​ኞ​ቹም በሮ​ቹን ሁሉ ይጠ​ብቁ ነበር፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሌዋ​ው​ያን ያዘ​ጋ​ጁ​ላ​ቸው ነበ​ርና ከአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ይርቁ ዘንድ አያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸ​ውም ነበር።


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።


ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ደቡብ ይመ​ለ​ከት ነበረ፤ ሌላ​ውም ወደ ደቡብ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከት ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos