አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
ዘኍል 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፤ ጠላቱ ኤሳው ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኀይል ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤዶም ይሸነፋል፤ ጠላቱ ሴይርም ድል ይሆናል፤ እስራኤል ግን እየበረታ ይሄዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤዶምን አሸንፎ የራሱ ያደርጋታል፤ ጠላቱ ሴርም የእርሱ ትሆናለች፤ እስራኤል ድል አድራጊ እንደ ሆነ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል። |
አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
መላዋን ኤዶምያስን ይጠብቁ ዘንድ በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮችን አኖረ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ጠበቀው።
እግዚአብሔርም ኤዶማዊው አዴርን ከረምማቴር ወገን የኤልያዳሔ ልጅ ኤስሮምን የሲባ ንጉሥ ጌታውን አድረዓዛርን ጠላት አድርጎ በሰሎሞን ላይ አስነሣ። ሰዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። የዓመፁም አበጋዝ እርሱ ነበር። ደማስቆንም እጅ አደረጋት። በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ በእስራኤል ላይ ጠላት ሆነ። ኤዶማዊው አዴርም ከኤዶምያስ ነገሥታት ዘር ነበር።
ዳዊትም ኤዶምያስን ባጠፋ ጊዜ፥ የሠራዊቱም አለቃ ኢዮአብ ተወግተው የሞቱትን ሊቀብር በወጣ ጊዜ፥ የኤዶምያስንም ወንድ ሁሉ በገደለ ጊዜ፥
ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ።
“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ቤት አነሣለሁ፤ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፤ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤
ይኸውም የቀሩ ሰዎችንና ስሜም የተጠራባቸውን አሕዛብን ሁሉ ይፈልጉ ዘንድ ነው” ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።
የኤዶምያስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታልፍም፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዋጋለን፤ በጦርም እቀበልህ ዘንድ እወጣለሁ” አለው።