በዚህች ምድር ተቀመጥ፤ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህችን ምድር ሁሉ ለአንተም፥ ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህም ለአብርሃም የማልሁለትን መሐላ ከአንተ ጋር አጸናለሁ።
ዘኍል 23:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንደ ሰው የሚታለል አይደለም። እንደ ሰው ልጅም የሚዛትበት አይደለም፤ እርሱ ያለውን አያደርገውምን? አይናገረውምን? አይፈጽመውምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይዋሽ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፤ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፤ ተናግሮ አያደርገውምን? ተስፋ ሰጥቶስ አይፈጽመውምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንደ ሰው አይዋሽም፤ ሐሳቡንም እንደ ሰው አይለውጥም የሰጠውን ተስፋ ሁሉ ይፈጽማል፤ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን? |
በዚህች ምድር ተቀመጥ፤ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህችን ምድር ሁሉ ለአንተም፥ ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህም ለአብርሃም የማልሁለትን መሐላ ከአንተ ጋር አጸናለሁ።
እነሆም፥ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚያችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”
እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ከኢዮርብዓም ወገን በከተማዪቱ ውስጥ የሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳውም የሞተውን የሰማይ ወፎች ይበሉታል።
ለኢዩ፥ “ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ” ተብሎ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እንዲሁም ሆነ።
ንጉሡም በእጁ ተደግፎት የሚቆም የነበረ ያ ብላቴና ለኤልሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ የእህል ሿሿቴ ቢያደርግ ይህ ነገር ይሆናልን?” አለው። ኤልሳዕም፥ “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፤ ከዚያ ግን አትቀምስም” አለ።
አምላክ ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ ስለ አገልጋይህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። አቤቱ፥ አምላክ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ።
ከቀስተኞች ቍጥር የቀሩት፥ የቄዳር ልጆች ኀያላን፥ ያንሳሉ፤” የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።
እርሱ ግን ጠቢብ ነው፤ ክፉንም ነገር በላያቸው ያመጣል፤ ቃሉንም አይመልስም፤ በክፉዎችም ሰዎች ቤት ላይ በከንቱ ተስፋቸውም ላይ ይነሣል።
ከምሥራቅና ከሩቅ ሀገር ስለ መከርሁት ምክር ዎፍን እጠራለሁ፤ ተናገርሁ፤ አመጣሁም፤ ፈጠርሁ፤ አደረግሁም፤ አመጣሁት፤ መንገዱንም አቀናሁለት።
ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ነው፤ የምሻውን እስኪያደርግ ድረስ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም፤ መንገዴንና ትእዛዜን አከናውናለሁ።
ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፤ በላይም ሰማይ ይጠቍራል፤ ተናግሬአለሁና፤ አልጸጸትም ወደፊት እሮጣለሁ፤ ከእርስዋም አልመለስም።
እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካካልህም ቅዱሱ ነኝና እንግዲህ የቍጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፤ ኤፍሬምንም ያጠፉት ዘንድ አልተውም፤ ወደ ከተማም አልገባም አልሁ።
ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፣ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፣ እርሱ አይዘገይም።
እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፤ በዚያም ይሞታሉ።”
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።
በመሐላ የሾመውን ግን፥ “እግዚአብሔር ማለ፥ አይጸጸትምም፤ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘለዓለም ካህን ነህ” አለው።
በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
እስራኤል ለሁለት ይከፈላል፤ ከእንግዲህም አይሰበሰብም፤ እግዚአብሔርም እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይጸጸትም” አለው።