“የሰውን አዝመራ ከብቱን ያስበላ፥ የሌላ ሰው ወይንንም ያስበላ ሰው ቢኖር ግምቱን ይክፈል። የሰውን አዝመራ ፈጽሞ ቢያስበላ ግን በአጠገቡ ባለ አዝመራ ልክ ይክፈል፤ ወይንም ቢሆን በአጠገቡ ባለ ወይን ልክ ይክፈል።
ዘኍል 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ አለቃ ነህን? ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አገባኸንን? እርሻንና የወይን ቦታንስ አወረስኸንን? የእነዚህንስ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በቀር አንተ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ምድር አላመጣኸንም፤ ወይም ዕርሻዎችንና የወይን ተክል ቦታዎች አላወረስኸንም። ታዲያ የእነዚህን ሰዎች ዐይን ታወጣለህን? በጭራሽ አንመጣም!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላስገባኸንም፥ እርሻና የወይንም ተክል ቦታ አላወረስከንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለም ወደሆነችው ምድር እንዳላመጣኸን ወይም የእርሻና የወይን ተክል ቦታ እንዳላወረስከን የተረጋገጠ ነው፤ አሁን ደግሞ ልታታልለን ትፈልጋለህ፤ እንግዲህስ ወደ አንተ አንመጣም!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላገባኸንም፥ እርሻና ወይንም አላወረስኸንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዓይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም አሉ። |
“የሰውን አዝመራ ከብቱን ያስበላ፥ የሌላ ሰው ወይንንም ያስበላ ሰው ቢኖር ግምቱን ይክፈል። የሰውን አዝመራ ፈጽሞ ቢያስበላ ግን በአጠገቡ ባለ አዝመራ ልክ ይክፈል፤ ወይንም ቢሆን በአጠገቡ ባለ ወይን ልክ ይክፈል።
በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳርፋትም፤ የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ።
እንዲህም አልሁ፦ ከግብፅ መከራ ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኬጤዎናውያን፥ ወደ አሞሬዎናውያን፥ ወደ ፌርዜዎናውያን፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያን፥ ወደ ኤዌዎናውያን፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያን ሀገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ሀገር አወጣችኋለሁ፤
ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም ሀገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊዪቱና ወደ መልካሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
ነገር ግን እናንተ፦ ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ፤ እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።
ዘር ወደማይዘራበት፥ በለስና ወይንም፥ ሮማንም፥ የሚጠጣም ውኃ ወደሌለበት ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን?”
ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዐይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አውርደው በእግር ብረት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።
አሞናዊው ናዖስም፦“ ቀኝ ዐይናችሁን ብታወጡ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብን አደርጋለሁ” አላቸው።