Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ይዘው ዐይ​ኖ​ቹን አወ​ጡት፤ ወደ ጋዛም አው​ር​ደው በእ​ግር ብረት አሰ​ሩት፤ በግ​ዞ​ትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዓይኖቹን አወጡት፥ ወደ ጋዛም አምጥተው በናስ ሰንሰለት አሰሩት፥ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 16:21
15 Referencias Cruzadas  

የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ልጆች በፊቱ ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይ​ኖች አወጡ፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አሰ​ሩት፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ወሰ​ዱት።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ሠራ​ዊት አለ​ቆች አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ምና​ሴ​ንም በዛ​ን​ጅር ያዙት፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዱት።


ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ግር ብረት፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ን​ሰ​ለት ያስ​ራ​ቸው ዘንድ፤


በግ​ብ​ፅም ሀገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙ​ፋኑ ከሚ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ በወ​ፍጮ እግር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አገ​ል​ጋ​ዪቱ በኵር ድረስ፥ የከ​ብ​ቱም በኵር ሁሉ ይሞ​ታል።


ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል።


ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ ቀና መንገዶችንም አያገኙም፥ ሕይወት በአለው ዘመንም አይገኙም።


ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ ሁሉም በኀጢአቱ ልባብ ይታሰራል።


ወፍጮ ወስ​ደሽ ዱቄ​ትን ፍጪ፤ ክን​ብ​ን​ብ​ሽን ግለጪ፤ ሽበ​ትሽ ይታይ፤ ባት​ሽን ግለጪ፤ ወን​ዙ​ንም ተሻ​ገሪ።


የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይን አወጣ፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስሮ ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ደው።


ጐል​ማ​ሶች ወፍ​ጮን ተሸ​ከሙ፤ ልጆ​ችም በእ​ን​ጨት ደከሙ።


አንተ አለቃ ነህን? ደግ​ሞስ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር አገ​ባ​ኸ​ንን? እር​ሻ​ንና የወ​ይን ቦታ​ንስ አወ​ረ​ስ​ኸ​ንን? የእ​ነ​ዚ​ህ​ንስ ሰዎች ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ታወ​ጣ​ለ​ህን? አን​መ​ጣም” አሉ።


ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች።


ደሊ​ላም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቅቶ፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወት​ሮ​ውም ጊዜ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም” አለ። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ እንደ ተለ​የው አላ​ወ​ቀም።


የራ​ሱም ጠጕር ከላ​ጩት በኋላ ያድግ ጀመር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos