ዘኍል 14:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚያችም ምድር ክፉን ነገር ተናገሩ፤ ስለዚያችም ምድር ክፉ የተናገሩ እነዚያ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት ሞቱ፤ ምድሪቱ ግን መልካም ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ምድሪቱም ክፉ ወሬ በማሠራጨት ተጠያቂ የሆኑት እነዚሁ ሰዎች ተቀሥፈው በእግዚአብሔር ፊት ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያ ክፉ ወሬ ስለ ምድሪቱ ያወሩ ሰዎች በጌታ ፊት በመቅሠፍት ሞቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት ተቀሥፈው ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉ ወሬ ያወሩ እነዚያ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት ሞቱ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሔልማዊውን ሸማያንና ዘሩን እቀጣለሁ፤ እኔም ለሕዝቤ የማደርገውን መልካሙን ነገር የሚያይ ሰው በመካከላችሁ አይኖርላቸውም፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በእግዚአብሔር ላይ ዐመፃን ተናግሮአልና።”
ስለ ሰለሉአትም ምድር ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፥ “እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው፤
በሞት እቀጣቸዋለሁ፤ አጠፋቸዋለሁም፤ አንተንና የአባትህን ቤት ግን ለታላቅና ከዚህ ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ” አለው።
ሙሴንም ተጣሉት፤ እንዲህም ብለው ተናገሩት፥ “ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ፤
አህያዪቱም አይታኝ ከፊቴ ፈቀቅ አለች፤ ይህም ሦስተኛ ጊዜ ነው፤ ከፊቴስ ፈቀቅ ባላለች በእውነት አሁን አንተን በገደልሁህ፤ እርሷንም ባዳንኋት ነበር” አለው።
ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።