Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ይሁዳ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ምንም እንኳ አስቀድማችሁ ይህን ሁሉ የምታውቁ ቢሆንም፣ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ ምድር እንዴት እንዳወጣ፣ በኋላ ግን ያላመኑትን እንዳጠፋ ላስታውሳችሁ እወድዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ነገር ግን ሁሉን ነገር አንድ ጊዜ ያወቃችሁትን እናንተን፥ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ይህን ሁሉ አስቀድማችሁ አንድ ጊዜ የምታውቁት ቢሆንም እንኳ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አውጥቶ እንዳዳነና ያላመኑትንም በኋላ እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ይሁዳ 1:5
14 Referencias Cruzadas  

ወደ ሰማይ ይወ​ጣሉ፥ ወደ ጥል​ቅም ይወ​ር​ዳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም በመ​ከራ ቀለ​ጠች።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አገ​ኘ​ሁት ጸጋ ላሳ​ስ​ባ​ችሁ በአ​ን​ዳ​ንድ ቦታ በድ​ፍ​ረት ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።


ዳሩ ግን በዚህ ነገር አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ትም።


ሰም​ተው ያሳ​ዘ​ኑ​ትስ እነ​ማን ናቸው? በሙሴ እጅ ከግ​ብፅ የወ​ጡት ሁሉ አይ​ደ​ሉ​ምን?


ወዳጆች ሆይ! አሁን የምጽፍላችሁ መልእክት ይህች ሁለተኛይቱ ናት። በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለውን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችኋትን የጌታችንንና የመድኃኒታችንን ትእዛዝ እንድታስቡ በሁለቱ እያሳሰብኋችሁ ቅን ልቡናችሁን አነቃቃለሁ።


እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።


እውነትን የምታውቁ ስለ ሆናችሁ፥ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን ስለማታውቁ አልጽፍላችሁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos