ዘኍል 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም በክፋት በእግዚአብሔር ፊት አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ በእነርሱ ላይ ነደደች፤ ከሰፈሩም አንዱን ወገን በላች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ስለ ደረሰባቸው ችግር በእግዚአብሔር ላይ አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ማጕረምረማቸውን በሰማ ጊዜ በጣም ተቈጣ፤ ከዚያም የእግዚአብሔር እሳት በመካከላቸው ነደደች፤ ከሰፈሩም ዳርቻ ጥቂቱን በላች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ስለ ደረሰባቸው መከራ በጌታ ላይ አጉረመረሙ፤ ጌታም ሰምቶ እጅግ ተቈጣ፤ የጌታም እሳት በመካከላቸው ነደደ፥ የሰፈሩንም ዳር በላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ክፉ ሆነው በእግዚአብሔር ላይ አጉረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ነደደች፥ የሰፈሩንም ዳር በላች። |
የልቅሶዋም ወራት ሲፈጸም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስትም ሆነችው፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሆነ።
ኤልያስም፥ “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ” አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎች በላች።
እርሱም ገና ይህን ሲናገር ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፦ ለኢዮብ እንዲህ አለው፥ “እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎችህንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችህንም በላች፤ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ።”
የእግዚአብሔርንም ክብር ጥዋት ታያላችሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ያንጐራጐራችሁትን ሰምቶአልና፤ በእኛም ላይ የምታንጐራጕሩ እኛ ምንድን ነን?” አሉ።
ሙሴም አሮንን፥ “ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ‘ማንጐራጐራችሁን ሰምቶአልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎችን ያዘ፤ እሳት እንደሚነድድ የሚነግራችሁ ማን ነው? የዘለዓለም ሀገርንስ የሚነግራችሁ ማን ነው?
በግብፅ ምድረ በዳ ከአባቶቻችሁ ጋር እንደ ተፋረድሁ እንዲሁ ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድሩበትን ቦታ ታገኝላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ትቀድማቸው ነበር።
ሕዝቡንም በላቸው፦ ሥጋ ማን ያበላናል? በግብፅ ደኅና ነበረልን እያላችሁ በእግዚአብሔር ፊት አልቅሳችኋልና ለነገ ተቀደሱ፤ ሥጋንም ትበላላችሁ፤ እግዚአብሔርም ሥጋን ይሰጣችኋል፤ ትበሉማላችሁ።
እነርሱም፥ “በውኑ እግዚአብሔር በሙሴ ብቻ ተናግሮአልን? በእኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን?” አሉ፤ እግዚአብሔርም ሰማ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከምንሞት በግብፅ ምድር ሳለን ብንሞት በተሻለን ነበር።
በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥ ቃሌንም ስላልሰሙ፥
“የሚያጕረመርሙብኝን እኒህን ክፉ ማኅበር እስከ መቼ እታገሣቸዋለሁ? ስለ እናንተ በእኔ ላይ የሚያጕረመርሙትን የእስራኤል ልጆች ማጕረምረምን ሰማሁ።
እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህም አንተና ማኅበርህ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ተሰብስባችኋል፤ በእርሱም ላይ ታጕረመርሙ ዘንድ አሮን ማንነው?”
እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ትለመልማለች፤ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁ የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።”
ሕዝቡም፥ “በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣኸን?” ብለው እግዚአብሔርንና ሙሴንም አሙ። “እንጀራ የለም፤ ውኃም የለምና፥ ሰውነታችንም ይህን ጥቅም የሌለው እንጀራ ተጸየፈች” ብለው ተናገሩ።
በመንገድ ላይ እንደ ተቃወመህ፥ አንተም ተርበህና ደክመህ ሳለህ ጓዝህንና ከአንተ በኋላ ደክመው የነበሩትን ሁሉ እንደ መታ፤ እግዚአብሔርንም አልፈራውም።
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።
እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።