Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሌላ መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፦ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “እሳት ከሰ​ማይ ወደ​ቀች፥ በጎ​ች​ህ​ንም አቃ​ጠ​ለች፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ህ​ንም በላች፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወረደች፤ በጎችንና አገልጋዮችንም በላች፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ “የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎቹንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችንም በላች፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የመጀመሪያው መልእክተኛ ንግግሩን ገና ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጣና “በጎቹንና እረኞቹን በሙሉ መብረቅ ከሰማይ ወርዶ ገደላቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎቹንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችንም በላች፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 1:16
13 Referencias Cruzadas  

ኤል​ያ​ስም፥ “እኔስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰ​ማይ ትው​ረድ፤ አን​ተ​ንም፥ አም​ሳ​ው​ንም ሰዎ​ች​ህን ትብላ” አለው። እሳ​ትም ከሰ​ማይ ወርዳ እር​ሱ​ንና አም​ሳ​ውን ሰዎች በላች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ዶ​ምና በገ​ሞራ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን አዘ​ነበ፤


እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ፍ​ረድ በቃሉ እሳ​ትን ጠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቁን ቀላ​ይና ምድ​ርን በላች።


ኤል​ያ​ስም መልሶ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውን፥ “እኔስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰ​ማይ ትው​ረድ፤ አን​ተ​ንም፥ አም​ሳ​ው​ንም ሰዎ​ች​ህን ትብላ” አለው። እሳ​ትም ከሰ​ማይ ወርዳ እር​ሱ​ንና አም​ሳ​ውን ሰዎች በላች።


እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች።


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥቶ በላ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ሞቱ።


እነሆ፥ እሳት ከሰ​ማይ ወርዳ የፊ​ተ​ኞ​ቹን ሁለ​ቱን የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችና አምሳ አም​ሳ​ውን ሰዎ​ቻ​ቸ​ውን በላች፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊ​ትህ የከ​በ​ረች ትሁን።”


በሰ​ፈ​ሩና በእ​ር​ሻ​ውም ድን​ጋጤ ሆነ፤ በሰ​ፈሩ የተ​ቀ​መጡ ሕዝ​ብና የሚ​ዋ​ጉ​ትም ሁሉ ተሸ​በሩ፤ መዋ​ጋ​ትም አል​ቻ​ሉም፤ ምድ​ሪ​ቱም ተና​ወ​ጠች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ታላቅ ድን​ጋጤ መጣ።


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ስቡ​ንም በላ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው ተደ​ነቁ፤ በግ​ም​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደቁ።


እን​ግ​ዲህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ የአ​ም​ላክ ነጐ​ድ​ጓድ፥ በረ​ዶ​ውም፥ እሳ​ቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከዚህ አት​ቀ​መ​ጡም” አላ​ቸው።


ውኆ​ቻ​ቸው ጮኹ ደፈ​ረ​ሱም፥ ተራ​ሮ​ችም ከኀ​ይሉ የተ​ነሣ ተና​ወጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios