እነርሱም አሉ፥ “ባሪያዎችህ በከነዓን ምድር የምንኖር ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፤ ሌላውም ሞቶአል።”
ዘኍል 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ |
እነርሱም አሉ፥ “ባሪያዎችህ በከነዓን ምድር የምንኖር ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፤ ሌላውም ሞቶአል።”
ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።
እነሆም፥ ንጉሡን እንደ ተለመደው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ፥ ከንጉሡም ጋር መዘምራንና መለከተኞች ቆመው አየች፤ የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከት ይነፉ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች።
እነሆም፥ ንጉሡ በመግቢያው በዓምዱ አጠገብ ሆኖ በንጉሡም ዙሪያ አለቆችና መለከተኞች፥ መኳንንትም ቆመው አየች። ሕዝቡም ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከቱን ይነፉ ነበር፤ መዘምራንም በዜማ ዕቃ እያዜሙ የምስጋና መዝሙር ይዘምሩ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።
መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ ከአሳፍና ከኤማን፥ ከኤዶትምም ልጆች ጋር ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና ከበሮ፥ መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር።
ካህናቱም በየሥርዐታቸው ሌዋውያኑም ደግሞ፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግዚአብሔርን ለማመስገን የሠራውን የእግዚአብሔርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር።
አናጢዎቹም የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠሩ ዘንድ መሠረት በጣሉ ጊዜ ካህናቱ ልብሳቸውን ለብሰው መለከቱን ይዘው፥ የአሳፍም ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው እንደ እስራኤል ንጉሥ እንደ ዳዊት ሥርዐት እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ቆሙ።
ሙሴና አሮን በክህነታቸው ቅዱሳን ናቸውና ሳሙኤልም ስሙን ከሚጠሩት ጋራ፤ እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።
“በሰባተኛውም ወር ከወሩ የመጀመሪያዋ ቀን ለእናንተ ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ምልክት ያለባት ቀን ትሁንላችሁ።
ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል አለቆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ቍርባናቸውን አቀረቡ፤ እነዚህም ከተቈጠሩት በላይ የተሾሙ የነገዶች አለቆች ነበሩ።
በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፤ እግዚአብሔር በሙሴ ቃል እንደ አዘዘ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።
ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።
ሦስቱም ወገኖች ቀንደ መለከቶችን ነፉ፤ ማሰሮዎችንም ሰበሩ፤ በግራ እጃቸውም ችቦዎችን፥ በቀኝ እጃቸውም ቀንደ መለከቶችን ይዘው እየነፉ፥ “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ።