Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 98 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ፥ ምድ​ርን አነ​ዋ​ወ​ጣት።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ታላቅ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

3 ሁሉ ታላቅ ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናል፥ ግሩ​ምና ቅዱስ ነውና።

4 ክቡር ንጉሥ ፍር​ድን ይወ​ድ​ዳል፤ አንተ በኀ​ይ​ልህ ጽድ​ቅን አጸ​ናህ፥ ለያ​ዕ​ቆብ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አንተ አደ​ረ​ግህ።

5 ፈጣ​ሪ​ያ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አለ፥ ከእ​ግሩ መረ​ገጫ በታ​ችም ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል።

6 ሙሴና አሮን በክ​ህ​ነ​ታ​ቸው ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና ሳሙ​ኤ​ልም ስሙን ከሚ​ጠ​ሩት ጋራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠሩት፥ እር​ሱም መለ​ሰ​ላ​ቸው።

7 በደ​መና ዐም​ድም ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ምስ​ክ​ሩ​ንና የሰ​ጣ​ቸ​ውን ትእ​ዛዝ ጠበቁ።

8 አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ ሰማ​ሃ​ቸው፤ አቤቱ፥ አንተ ማር​ሃ​ቸው፥ በሥ​ራ​ቸው ሁሉ ግን ትበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።

9 አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራራ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነውና።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos