Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ካህ​ና​ቱም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ኑም ደግሞ፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ለ​ውን የዳ​ዊ​ትን መዝ​ሙር እየ​ዘ​መሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገን የሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህ​ና​ቱም በፊ​ታ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ቆመው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ካህናቱም እንደ ሌዋውያኑ፣ ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔር እንዲወደስበት የሠራውንና “ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል” በማለት እግዚአብሔርን ባመሰገነ ጊዜ፣ የተቀመጠበትን የእግዚአብሔርን የዜማ መሣሪያ ይዘው በተመደበላቸው ስፍራ ቆሙ። ካህናቱ በሌዋውያኑ ትይዩ ሆነው መለከቶቻቸውን ሲነፉም እስራኤላውያን ሁሉ ቆመው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ካህናቱም በየሥርዓታቸው፥ ሌዋውያኑም ደግሞ፦ ጽኑ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት ጌታን ለማመስገን የሠራውን የጌታን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ካህናቱም በተመደበላቸው ቦታ ቆሙ፤ ከእነርሱም ፊት ለፊት ሌዋውያን ቆመው አስቀድሞ ንጉሥ ዳዊት አሠርቶ እግዚአብሔርን ለማመስገን ይጠቀምባቸው በነበሩት የዜማ መሣሪያዎች ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በመዘመር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ካህናቱም መለከት ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆመው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ካህናቱም በየሥርዓታቸው፥ ሌዋውያኑም ደግሞ “ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤” የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግዚአብሔርን ለማመስገን የሠራውን የእግዚአብሔርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 7:6
26 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከመ​ዘ​ም​ራን ጋር በበ​ገና፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በከ​በሮ፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በመ​ለ​ከት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይዘ​ምሩ ነበር።


ካህ​ና​ቱም ሰበ​ንያ፥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ ናት​ና​ኤል፥ ዓማ​ሣይ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ በና​ያስ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት መለ​ከት ይነፉ ነበር። አብ​ዲ​ዶ​ምና ኢያ​ኤ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት በረ​ኞች ነበሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ። ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።


ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻ​ፈው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በደ​ስ​ታና በመ​ዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የከ​ፈ​ላ​ቸ​ውን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ሾመ።


ይህ​ንም ትእ​ዛዝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያቱ እጅ አዝ​ዞ​አ​ልና እንደ ዳዊ​ትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢ​ዩም እንደ ናታን ትእ​ዛዝ፥ ጸና​ጽ​ልና በገና፥ መሰ​ን​ቆም አስ​ይዞ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቆመ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አሳ​ርጉ” አለ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረግ በተ​ጀ​መረ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዝ​ሙር ደግሞ ተጀ​መረ፤ መለ​ከ​ቱም ተነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የዳ​ዊት ዜማ ዕቃ ተመታ።


መዘ​ም​ራ​ንም የነ​በ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ሁሉ፥ ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን፥ ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች ጋር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጥሩ በፍታ ለብ​ሰው ጸና​ጽ​ልና ከበሮ፥ መሰ​ን​ቆም እየ​መቱ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በም​ሥ​ራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መቶ ሃያ ካህ​ናት መለ​ከት ይነፉ ነበር።


መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ መዘ​ም​ራኑ በአ​ን​ድ​ነት ሆነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” እያሉ በአ​ንድ ቃል ድም​ፃ​ቸ​ውን ወደ ላይ ከፍ አድ​ር​ገው በመ​ለ​ከ​ትና በጸ​ና​ጽል፥ በዜ​ማም ዕቃ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባመ​ሰ​ገኑ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ብሩ ደመና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወ​ርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድን​ጋይ በተ​ነ​ጠ​ፈ​በ​ትም ምድር በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።


በዚ​ያ​ችም ዕለት ንጉሡ ሰሎ​ሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን ሠዋ። እን​ዲሁ ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቅዳሴ አከ​በሩ።


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።


ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑዕ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም።


ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደ ጥል​ቁም ብወ​ርድ፥ አንተ በዚያ አለህ፤


በእኔ ላይ ቍጣህ ጸና፥ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ሁሉ በእኔ ላይ አመ​ጣህ።


ስለ​ዚህ ሕዝቤ ስሜን ያው​ቃል፤ የም​ና​ገ​ርና ያለሁ እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያው​ቃሉ።”


ከበ​ገ​ናው ድምፅ ጋር አስ​ተ​ባ​ብ​ረው ለሚ​ያ​ጨ​በ​ጭቡ ሰዎች፤ ይኸ​ውም የማ​ያ​ልፍ ለሚ​መ​ስ​ላ​ቸ​ውና እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ቸው ለማ​ያ​ውቁ፤


ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት በታ​ቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይንፉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos