ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ዕቃዎቹንም ሁሉ ኪራም ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ሠራ። በንጉሡ ቤትና በእግዚአብሔር ቤትም አርባ ስምንት አዕማድ ነበሩ። ኪራምም ለንጉሡ የሠራቸው ዕቃዎች ሁሉ ከጥሩ ናስ ነበር።
ነህምያ 7:70 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአባቶች ቤቶች አለቆችም ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዥውም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባቶች አለቆች ለሥራው ለግምጃ ቤት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ምናን ብር ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎችም ቤተ መቅደሱን እንደገና ለመሥራት የሚረዳ አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ ከእነርሱም መካከል፥ አገረ ገዢው፦ 8 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 50 ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ 530 የካህናት ልብሶችን ሰጠ። የጐሣ አለቆችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1250 ኪሎ የሚመዝን ብር ሰጡ፤ የቀሩት ሰዎችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1100 ኪሎ የሚመዝን ብርና 67 የካህናት ልብሶችን ሰጥተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ ሰዎች ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ። |
ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ዕቃዎቹንም ሁሉ ኪራም ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ሠራ። በንጉሡ ቤትና በእግዚአብሔር ቤትም አርባ ስምንት አዕማድ ነበሩ። ኪራምም ለንጉሡ የሠራቸው ዕቃዎች ሁሉ ከጥሩ ናስ ነበር።
ለሥጋ ሜንጦዎቹና ለድስቶቹ፥ ለመጠጥ ቍርባን መቅጃዎቹም ጥሩውን ወርቅ፥ ለወርቁም ጽዋዎች ወርቁን በየጽዋው ሁሉ በሚዛን ሰጠው፤ ለብሩም ጽዋዎች ብሩን በየጽዋው በሚዛን ሰጠው።
ኪራምም ምንቸቶቹንና መጫሪያዎቹን፥ በመሠዊያው ቤት ያሉ ማንኪያዎችንና የመገልገያውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራምም ለንጉሡ ለሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።
ዐሥሩንም የወርቅ ገበታዎች ሠርቶ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው። አንድ መቶም የወርቅ ጽዋዎችን ሠራ።
ከአባቶች ቤቶች አለቆችም ዐያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሃያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ።
ሕቴርሰታ ነህምያም፥ ጸሓፊውም ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝቡንም የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፥ “ዛሬ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ነው፤ አትዘኑ፤ አታልቅሱም” አሉአቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና።
ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፤ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፤ በዕቃውም ውስጥ ከአለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ፤ ከእናንተም አንድ ሰው እስኪነጋ ድረስ ከቤቱ ደጅ አይውጣ።
የአዛዦችም አለቃ ጽዋዎቹን፥ ማንደጃዎቹን፥ ድስቶቹንና ምንቸቶቹን፥ መቅረዞቹንና ጭልፋዎቹን፥ መንቀሎችንም፥ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፥ የብሩንም ዕቃ በብር አድርጎ፥ ወሰደ።