Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


1 ነገሥት 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሰሎ​ሞን ቤተ መን​ግ​ሥ​ቱን እንደ ሠራ

1 ሰሎ​ሞ​ንም የራ​ሱን ቤት በዐ​ሥራ ሦስት ዓመት ሠራ፤ የቤ​ቱ​ንም ሥራ ሁሉ ጨረሰ።

2 የሊ​ባ​ኖስ ዱር ቤት የሚ​ባል ቤት​ንም ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንም መቶ ክንድ፥ ስፋ​ቱ​ንም አምሳ ክንድ፥ ቁመ​ቱ​ንም ሠላሳ ክንድ አደ​ረገ፤ የዋ​ን​ዛም እን​ጨት በሦ​ስት ወገን በተ​ሠሩ አዕ​ማድ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ዕ​ማ​ዱም ላይ የዋ​ንዛ እን​ጨት አግ​ዳሚ ሰረ​ገ​ሎች ነበሩ።

3 በአ​ዕ​ማ​ዱም ላይ በነ​በሩ አግ​ዳ​ሚ​ዎች ቤቱ በዋ​ንዛ ሳንቃ ተሸ​ፍኖ ነበር፤ አዕ​ማ​ዱም በአ​ንዱ ወገን ዐሥራ አም​ስት፥ በአ​ንዱ ወገን ዐሥራ አም​ስት የሆኑ አርባ አም​ስት ነበሩ።

4 መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ነበሩ፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ፊት ለፊት ይተ​ያዩ ነበር።

5 ደጆቹ፥ መቃ​ኖ​ቹና የታ​ች​ኛ​ውና የላ​ይ​ኛው መድ​ረ​ኮች ሁሉ አራት ማዕ​ዘን ነበሩ፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ሆነው ፊት ለፊት ይተ​ያዩ ነበር።

6 አዕ​ማ​ዱም ያሉ​በ​ትን ቤት ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ስፋ​ቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ፊት ደግሞ ታላቅ አዕ​ማ​ድና መድ​ረክ ያሉ​በት ወለል ነበረ።

7 የሚ​ፈ​ር​ድ​በ​ትም የቤቱ ዙፋን በዚያ አለ። ለመ​ፍ​ረ​ጃ​ውም ቤትን ሠራ፤ ከላይ እስከ ታችም በዋ​ንዛ እን​ጨት አያ​ያ​ዘው።

8 ከፍ​ርድ ሰቀላ ወደ ውስጥ፥ በሌ​ላ​ውም አደ​ባ​ባይ ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ቤት እን​ዲሁ ሠራ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ቤት ያለ ቤትን ሰሎ​ሞን ላገ​ባት ለፈ​ር​ዖን ልጅ ሠራ።

9 ይህም ሁሉ ከመ​ሠ​ረቱ ጀምሮ እስከ ጕል​ላቱ ድረስ በከ​በ​ረና በተ​ጠ​ረበ በው​ስ​ጥና በውጭ በልክ በተ​ከ​ረ​ከመ ድን​ጋይ ተሠ​ርቶ ነበር፤ በው​ጭ​ውም እስከ ታላቁ አደ​ባ​ባይ ድረስ እን​ዲሁ ነበረ።

10 መሠ​ረ​ቱም ዐሥር ዐሥር ክን​ድና ስም​ንት ስም​ንት ክንድ በሆኑ በከ​በሩ በታ​ላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮች ተሠ​ርቶ ነበር።

11 በላ​ዩም ልክ ሆኖ የተ​ከ​ረ​ከመ ጥሩ ድን​ጋ​ይና የዝ​ግባ ሣንቃ ነበረ።

12 በታ​ላ​ቁም አደ​ባ​ባይ ዙሪያ የነ​በ​ረው ቅጥር እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ቅጥ​ርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ አን​ዱም ወገን በዝ​ግባ ሳንቃ ተሠ​ርቶ ነበር።

13 ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ልኮ ኪራ​ምን ከጢ​ሮስ አስ​መጣ።

14 እር​ሱም ከን​ፍ​ታ​ሌም ወገን የነ​በ​ረች የባል አልባ ሴት ልጅ ነበረ፤ አባ​ቱም የጢ​ሮስ ሰው ናስ ሠራ​ተኛ ነበረ፤ የና​ስ​ንም ሥራ ሁሉ ይሠራ ዘንድ በጥ​በ​ብና በማ​ስ​ተ​ዋል፥ በብ​ል​ሃ​ትም ተሞ​ልቶ ነበር። ወደ ንጉ​ሡም ወደ ሰሎ​ሞን መጥቶ ሥራ​ውን ሁሉ ሠራ።

15 በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለ​ቱን የናስ አዕ​ማድ ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፤ የዙ​ሪ​ያ​ውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓ​ም​ዱም ውፍ​ረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍ​ትም ነበረ። ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓምድ እን​ዲሁ ነበረ።

16 በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ እን​ዲ​ቀ​መጡ ከፈ​ሰሰ ናስ ሁለት ጕል​ላ​ትን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ።

17 በአ​ዕ​ማ​ዱም ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መር​በብ ሥራ አደ​ረገ፤ አን​ዱም መር​በብ ለአ​ንዱ ጕል​ላት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም መር​በብ ለሁ​ለ​ተ​ኛው ጕል​ላት ነበረ።

18 ሮማ​ኖ​ች​ንም ሠራ፤ በአ​ንድ ጕል​ላት ዙሪያ በሁ​ለት ተራ፥ በአ​ን​ድም መር​በብ ላይ ሁለት ተራ ነበረ፤ እን​ዲ​ሁም ለሁ​ለ​ተ​ኛው ጕል​ላት አደ​ረገ።

19 በወ​ለ​ሉም አዕ​ማድ በነ​በ​ሩት ጕል​ላ​ቶች ላይ የሱፍ አበባ የሚ​መ​ስል ሥራ አራት ክንድ አድ​ርጎ ቀረጸ።

20 በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ በነ​በ​ሩት ጕል​ላ​ቶች ላይ በመ​ር​በቡ ሥራ አጠ​ገብ ሮማ​ኖ​ቹን አደ​ረገ። ሮማ​ኖ​ቹም በአ​ንዱ ወገን ሁለት መቶ ነበሩ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት እን​ዲሁ ነበረ።

21 አዕ​ማ​ዱ​ንም በመ​ቅ​ደሱ ወለል አጠ​ገብ አቆ​ማ​ቸው፤ የቀ​ኙ​ንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግ​ራ​ው​ንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።

22 በአ​ዕ​ማ​ዱም ራስ ላይ የሱፍ አበባ የሚ​መ​ስል ሥራ አደ​ረገ። እን​ዲ​ሁም የአ​ዕ​ማዱ ሥራ ተጨ​ረሰ።

23 ከፈ​ሰ​ሰም ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመ​ቱም አም​ስት ክንድ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ሠላሳ ክንድ የሆነ ክብ ኩሬ ሠራ።

24 ከከ​ን​ፈ​ሩም በታች ለአ​ንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአ​ንድ ክን​ድም ዐሥር ጕብ​ጕ​ቦች አዞ​ረ​በት፤ ከን​ፈ​ሮ​ቹም እንደ ጽዋ ከን​ፈር ነበሩ። በው​ስ​ጡም አበ​ቦች በቅ​ለ​ው​በት ነበር። ውፍ​ረ​ቱም ስን​ዝር ነበር።

25 ኩሬ​ውም በዐ​ሥራ ሁለት በሬ​ዎች ምስል ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስ​ቱም ወደ ምዕ​ራብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከቱ ነበር። ኩሬ​ውም በላ​ያ​ቸው ነበረ፤ የሁ​ሉም ጀር​ባ​ቸው በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።

26 ውፍ​ረ​ቱም አንድ ጋት ነበረ። ከን​ፈ​ሩም እንደ ጽዋ ከን​ፈር ተሠ​ርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበ​ባ​ዎች ሆኖ ተከ​ር​ክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ይይዝ ነበር።

27 ዐሥ​ርም የናስ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም መቀ​መጫ ርዝ​መት አራት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሦስት ክንድ ነበረ።

28 መቀ​መ​ጫ​ዎ​ች​ንም እን​ዲሁ ሠራ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም አያ​ይዞ ሰን​በር ባለው ክፈፍ ሠራ​ቸው።

29 በክ​ፈ​ፎ​ቹም መካ​ከል በነ​በሩ ሰን​በ​ሮች ላይ አን​በ​ሳ​ዎ​ችና በሬ​ዎች፥ ኪሩ​ቤ​ልም ነበሩ፤ እን​ዲ​ሁም በክ​ፈ​ፎቹ ላይ ነበረ፤ ከአ​ን​በ​ሳ​ዎ​ቹና ከበ​ሬ​ዎቹ በታች ሻኩራ የሚ​መ​ስል ተን​ጠ​ል​ጥሎ ነበር።

30 በየ​መ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ሁሉ አራት የናስ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም የሚ​ዞ​ሩ​በ​ትን የናስ ወስ​ከ​ምት ሠራ፤ ከመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውም ሰን በታች በአ​ራቱ ማዕ​ዘን በኩል አራት በም​ስል የፈ​ሰሱ እግ​ሮች ነበሩ።

31 በክ​ፈ​ፉም ውስጥ የነ​በረ አን​ገት አንድ ክንድ ነበረ፤ አን​ገ​ቱም ድቡ​ል​ቡል ነበረ፤ ቁመ​ቱም ክንድ ተኩል ነበረ። በአ​ን​ገ​ቱም ላይ ቅርጽ ነበ​ረ​በት፤ ክፈፉ ግን አራት ማዕ​ዘን ነበረ እንጂ ድቡ​ል​ቡል አል​ነ​በ​ረም።

32 አራ​ቱም መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ከሰ​ን​በ​ሮቹ በታች ነበሩ፤ የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም ወስ​ከ​ምት በመ​ቀ​መ​ጫው ውስጥ ነበረ፤ የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሩም ቁመት ክንድ ተኩል ነበረ።

33 የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም ሥራ እንደ ሰረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵር ሥራ ነበረ፤ ወስ​ከ​ም​ቶ​ቹና የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ ክፈፍ፥ ቅት​ር​ቶ​ቹም፥ ወስ​ከ​ምቱ የሚ​ገ​ባ​በት ቧምቧ ሁሉ በም​ስል የፈ​ሰሰ ነበር።

34 በየ​አ​ን​ዳ​ን​ዱም መቀ​መጫ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን በኩል አራት ደገ​ፋ​ዎች ነበሩ፤ ደገ​ፋ​ዎ​ቹም ከመ​ቀ​መ​ጫው ጋር ተጋ​ጥ​መው ነበር።

35 በመ​ቀ​መ​ጫ​ውም ራስ ላይ ስን​ዝር የሚ​ሆን ድቡ​ል​ቡል ነገር ነበረ፤ በመ​ቀ​መ​ጫ​ውም ላይ የነ​በሩ መያ​ዣ​ዎ​ችና ሰን​በ​ሮች ከእ​ርሱ ጋር ይጋ​ጠሙ ነበረ፤ ከላ​ይም ክፍት ነበረ፤

36 በክ​ፈ​ፎ​ቻ​ቸ​ውም ኪሩ​ቤ​ልና አን​በ​ሶች የዘ​ን​ባባ ዛፎ​ችም ነበሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ፊት ለፊት በስ​ተ​ው​ስ​ጥና በዙ​ሪ​ያው ተያ​ይዞ ነበር።

37 እን​ዲ​ሁም ዐሥ​ሩን መቀ​መ​ጫ​ዎች ሠራ፤ ሁሉም በመ​ጠን፥ በን​ድ​ፍም ትክ​ክ​ሎች ነበሩ።

38 ዐሥ​ሩ​ንም የናስ መታ​ጠ​ቢያ ሰን ሠራ፤ አንዱ መታ​ጠ​ቢያ ሰን አርባ የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ያነሣ ነበር፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መታ​ጠ​ቢያ ሰን አራት ክንድ ነበረ፤ በዐ​ሥ​ሩም መቀ​መ​ጫ​ዎች ላይ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ አንድ መታ​ጠ​ቢያ ሰን ይቀ​መጥ ነበር።

39 አም​ስ​ቱ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች በቤቱ ቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በቤቱ ግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ኩሬ​ው​ንም በቤቱ ቀኝ በአ​ዜብ ፊት ለፊት በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ አኖ​ረው።


ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መገ​ል​ገያ ዕቃ​ዎ​ችን እንደ ሠራ
( 2ዜ.መ. 4፥11 ፤ 5፥1 )

40 ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ች​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ድስ​ቶ​ች​ንም ሠራ፤ ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።

41 ሁለ​ቱ​ንም አዕ​ማድ፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ኩብ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጕል​ላ​ቶች፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሁለ​ቱን መር​በ​ቦች፥

42 በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መር​በብ በሁ​ለት በሁ​ለት ተራ አድ​ርጎ ለሁ​ለቱ መር​በ​ቦች አራት መቶ ሮማ​ኖ​ችን አደ​ረገ።

43 ዐሥ​ሩ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች፥ በመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ላይ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ዐሥ​ሩን መታ​ጠ​ቢያ ሰን፥

44 አን​ዱ​ንም ኩሬ፥ ከኩ​ሬ​ውም በታች የሚ​ሆ​ኑ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን በሬ​ዎች፥

45 ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ ኪራም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሠራ። በን​ጉሡ ቤትና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም አርባ ስም​ንት አዕ​ማድ ነበሩ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ የሠ​ራ​ቸው ዕቃ​ዎች ሁሉ ከጥሩ ናስ ነበር።

46 በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሜዳ በሱ​ኮ​ትና በተ​ር​ታን መካ​ከል ባለው በወ​ፍ​ራሙ መሬት ውስጥ አስ​ፈ​ሰ​ሰው።

47 ይህ ሁሉ ሥራ ለተ​ሠ​ራ​በት ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ የና​ሱም ሚዛን ብዙ ነበ​ርና አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።

48 ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወ​ር​ቁን መሠ​ዊያ፥ የገ​ጹም ኅብ​ስት የነ​በ​ረ​በ​ትን የወ​ርቅ ገበታ፥

49 በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት አም​ስቱ በቀኝ፥ አም​ስ​ቱም በግራ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከጥሩ ወርቅ የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም መቅ​ረ​ዞች፥ የወ​ር​ቁ​ንም አበ​ባ​ዎ​ችና ቀን​ዲ​ሎች፥ መኮ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም፥

50 ከጥሩ ወር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽን​ሐ​ሖ​ችን፥ ለው​ስ​ጠ​ኛ​ውም ቤት ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅ​ደ​ሱም ደጆች የሚ​ሆ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ማጠ​ፊ​ያ​ዎች አሠራ።

51 እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos