Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለ​ቱን የናስ አዕ​ማድ ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፤ የዙ​ሪ​ያ​ውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓ​ም​ዱም ውፍ​ረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍ​ትም ነበረ። ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓምድ እን​ዲሁ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኪራም የእያንዳንዱ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ ዙሪያው ዐሥራ ሁለት ክንድ የሆነ፣ ሁለት የናስ ምሰሶዎች ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሑራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ስምንት ሜትር፥ የዙሪያ ስፋታቸው አምስት ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ውስጡ ክፍት የሆነ አራት ጣት ውፍረት ካለው ነሐስ ሁለት ምሰሶዎችን ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሑራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ስምንት ሜትር፥ የዙሪያ ስፋታቸው አምስት ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ውስጡ ክፍት የሆነ አራት ጣት ውፍረት ካለው ነሐስ ሁለት ምሰሶዎችን ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሁለቱን የናስ አዕማድ አደረገ፤ የአንዱም ዐምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዐምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዐምድ እንዲሁ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 7:15
13 Referencias Cruzadas  

ዐም​ዶ​ቹም፥ የአ​ንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፥ የዙ​ሪ​ያ​ውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍ​ረ​ቱም ጋት ያህል ነበረ፤ ባዶም ነበረ።


አዕ​ማ​ዱ​ንም በመ​ቅ​ደሱ ወለል አጠ​ገብ አቆ​ማ​ቸው፤ የቀ​ኙ​ንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግ​ራ​ው​ንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት አቃ​ጠለ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላ​ላ​ቆ​ችን ቤቶች ሁሉ፥ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


ሁለ​ቱ​ንም አዕ​ማድ፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ኩብ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጕል​ላ​ቶች፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሁለ​ቱን መር​በ​ቦች፥


በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ እን​ዲ​ቀ​መጡ ከፈ​ሰሰ ናስ ሁለት ጕል​ላ​ትን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ።


ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትን የናስ ዓም​ዶች፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የነ​በ​ሩ​ትን መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችና የናስ ኵሬ​ዎች ሰባ​በሩ፤ ናሱ​ንም ወደ ባቢ​ሎን ወሰዱ።


ስላ​ል​ወ​ሰ​ዳ​ቸው ዓም​ዶች፥ ስለ ባሕ​ሩም፥ ስለ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም፥ በዚች ከተማ ስለ ቀሩት ዕቃ​ዎች ሁሉ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦


ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ሩ​ትን የናስ ዐም​ዶች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የነ​በ​ሩ​ትን መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችና የና​ሱን ኩሬ ሰባ​በሩ፤ ናሱ​ንም ወደ ባቢ​ሎን ወሰዱ።


የደጀ ሰላ​ሙም ርዝ​መት ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፥ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ዐሥር ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ አንድ በዚህ ወገን፥ አን​ድም በዚያ ወገን ሆነው በመ​ቃ​ኖቹ አጠ​ገብ የግ​ንብ አዕ​ማድ ነበሩ።


ከሚ​ጢ​ብ​ሐ​ትና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚ​ህም ሰሎ​ሞን የና​ሱን ኩሬና ዓም​ዶች የና​ሱ​ንም ዕቃ ሠራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios