Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አዕ​ማ​ዱ​ንም በመ​ቅ​ደሱ ወለል አጠ​ገብ አቆ​ማ​ቸው፤ የቀ​ኙ​ንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግ​ራ​ው​ንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ዐምዶቹንም በቤተ መቅደሱ መመላለሻ ላይ አቆመ፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ዐምድ “ያኪን”፣ በስተሰሜን በኩል ያለውንም “ቦዔዝ” ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሑራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምሰሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፤ ከቤተ መቅደሱ መግቢያ በር በስተ ደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሰሶ ደግሞ ቦዔዝ ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሑራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምሰሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፤ ከቤተ መቅደሱ መግቢያ በር በስተ ደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሰሶ ደግሞ ቦዔዝ ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አዕማዱንም በመቅደሱ ወለል አጠገብ አቆማቸው፤ የቀኙንም ዐምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግራውንም ዐምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 7:21
14 Referencias Cruzadas  

ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።


በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ወለል ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ መቅ​ደሱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ከቤቱ ወደ ፊት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ ቤቱ​ንም ሠርቶ ጨረሰ።


በታ​ላ​ቁም አደ​ባ​ባይ ዙሪያ የነ​በ​ረው ቅጥር እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ቅጥ​ርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ አን​ዱም ወገን በዝ​ግባ ሳንቃ ተሠ​ርቶ ነበር።


በአ​ዕ​ማ​ዱም ራስ ላይ የሱፍ አበባ የሚ​መ​ስል ሥራ አደ​ረገ። እን​ዲ​ሁም የአ​ዕ​ማዱ ሥራ ተጨ​ረሰ።


አዕ​ማ​ዶ​ቹ​ንም አን​ደ​ኛ​ውን በቀኝ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ፊት አቆ​ማ​ቸው፤ በቀ​ኝም የነ​በ​ረ​ውን ስም ርትዕ በግ​ራም የነ​በ​ረ​ውን ስም ጽንዕ ብሎ ጠራ​ቸው።


በሁ​ለ​ቱም መር​በ​ቦች አራት መቶ የወ​ርቅ ሻኵ​ራ​ዎ​ች​ንና በዐ​ም​ዶቹ ላይ ያሉ​ትን ሁለት ጕል​ላ​ቶች በሁ​ለት ጎኖች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሮማ​ኖች ሠራ።


ክብ​ርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ርቁ ሁሉ ያፍ​ራሉ።


ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።


እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።


የሰ​ጠ​ኝ​ንም ጸጋ ዐው​ቀው አዕ​ማድ የሚ​ሏ​ቸው ያዕ​ቆ​ብና ኬፋ፥ ዮሐ​ን​ስም እኛ ወደ አሕ​ዛብ፥ እነ​ር​ሱም ወደ አይ​ሁድ እን​ድ​ን​ሄድ ለእ​ኔና ለበ​ር​ና​ባስ ቀኝ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።


ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።


አማትዋም፦ ዛሬ ወዴት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን አለቻት። እርስዋም፦ ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማትዋ ነገረቻት።


ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos