ነህምያ 7:70 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም70-72 አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎችም ቤተ መቅደሱን እንደገና ለመሥራት የሚረዳ አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ ከእነርሱም መካከል፥ አገረ ገዢው፦ 8 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 50 ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ 530 የካህናት ልብሶችን ሰጠ። የጐሣ አለቆችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1250 ኪሎ የሚመዝን ብር ሰጡ፤ የቀሩት ሰዎችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1100 ኪሎ የሚመዝን ብርና 67 የካህናት ልብሶችን ሰጥተዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም70 አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዥውም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)70 የአባቶች አለቆች ለሥራው ለግምጃ ቤት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ምናን ብር ሰጡ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)70 ከአባቶች ቤቶች አለቆችም ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)70 ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ ሰዎች ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ። Ver Capítulo |
ሑራም በተጨማሪ ምንቸቶችን፥ መጫሪያዎችንና ማንቈርቈሪያዎችንም ሠራ፤ በዚህ ሁኔታም ሑራም ለንጉሥ ሰሎሞን እንዲሠራለት ቃል በገባለት መሠረት ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውለውን ዕቃ ሁሉ ሠርቶ ፈጸመ፤ የሠራቸውም ዕቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፦ ሁለት ምሰሶዎች፥ በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ የሚገኙት የሳሕን ቅርጽ ያላቸው ሁለት ጒልላቶች፥ ሁለቱን ጉልላቶች ለማስጌጥ በእያንዳንዱ ጒልላት ላይ የሚገኙት በመርበብ አምሳል የተቀረጹት ሁለት ሰንሰለቶች፥ ጉልላቶቹን ለማስጌጥ በእያንዳንዱ ጒልላት ላይ በሁለት ዙር የተቀረጹ ከነሐስ የተሠሩ አራት መቶ የሮማን ፍሬ ምስሎች፥ ዐሥሩ ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎች፥ ዐሥሩ የመታጠቢያ ገንዳዎች፥ ትልቁ ገንዳ፥ በርሜሉን ደግፈው የያዙት የዐሥራ ሁለቱ በሬዎች ቅርጾች፥ ምንቸቶች፥ መጫሪያዎች፥ ሜንጦዎችና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ዕቃዎች በእጅ ጥበብ ሠራ። ታዋቂ የሆነው ሑራም በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ የሠራው ከተወለወለ ነሐስ ነበር።