ንጉሡም ሰሎሞን ለእናቱ መልሶ፥ “ሱነማዪቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኚለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት፤ ካህኑም አብያታርና የሶርህያ ልጅ የጭፍሮች አለቃ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው” አላት።
ማርቆስ 10:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፣ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም፥ “የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ የምጠጣውን (የመከራ) ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን? እኔስ የምጠመቀውን ጥምቀት መጠመቅ ትችላላችሁን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ ግን፦ የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አላቸው። |
ንጉሡም ሰሎሞን ለእናቱ መልሶ፥ “ሱነማዪቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኚለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት፤ ካህኑም አብያታርና የሶርህያ ልጅ የጭፍሮች አለቃ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው” አላት።
ለወገኑ የሚፈርድ አምላክሽ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ የሚያንገደግድሽን ጽዋ የቍጣዬንም ጽዋ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፥ “ያልተበረዘ የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አንተን የምሰድድባቸውን አሕዛብን ሁሉ አጠጣቸው።
ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ እነሆ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልጋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።”
ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ “አባቴ! ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን፤” አለ።
እንዲህም አለ፥ “አባት ሆይ፥ ብትፈቅድስ ይህን ጽዋ ከእኔ አሳልፈው፤ ነገር ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን።”
መንፈስ ቅዱስም ከድካማችን ይረዳናል፤ እንግዲያስ ተስፋችንን ካላወቅን ጸሎታችን ምንድነው? ነገር ግን እርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ስለ መከራችንና ስለ ችግራችን ይፈርድልናል።