Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ያዕቆብ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፣ ለራሳችሁ ሥጋዊ ደስታ በማሰብ በክፉ ምኞት ትለምናላችሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የምትለምኑትም ለፍትወታችሁ በማሰብ በክፉ ምኞት ስለሆነ፥ ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ብትጸልዩም የጸሎታችሁን መልስ የማታገኙት የለመናችሁትን ነገር በሥጋዊ ደስታ ላይ ለማዋል በክፉ ሐሳብ ስለምትጸልዩ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።

Ver Capítulo Copiar




ያዕቆብ 4:3
25 Referencias Cruzadas  

በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።


ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በአካላችሁ ክፍሎች ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?


የዚያን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፥ እርሱም አይሰማቸውም፥ ሥራቸውንም ክፉ አድርገዋልና በዚያን ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል።


የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


ድሃን እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጣራል፥ የሚሰማውም የለም።


በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ስድብ ይጮ​ኻሉ፥ እርሱ ግን አይ​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


እኔ በጠራሁ ጊዜ እነርሱ እንዳልሰሙኝ፥ እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩበት ጊዜ እኔ አልሰማም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ያ ትንሹ ልጁ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ በዚ​ያም በመ​ዳ​ራት እየ​ኖረ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ በተነ፤ አጠ​ፋም።


ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አላቸው።


ኢየሱስ ግን መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አለ። “እንችላለን” አሉት።


አን​ተም ስለ​ዚህ ሕዝብ አት​ጸ​ልይ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ቀን ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምና ስለ እነ​ርሱ አት​ጸ​ልይ፤ በም​ል​ጃና በጸ​ሎት አት​ማ​ልድ።


የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በክፋት ያቀርቡታልና።


ግን በጠራችሁኝ ጊዜ እኔ አልሰማችሁም፤ ክፉዎች ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።


ቢጾሙ ጸሎ​ታ​ቸ​ውን አል​ሰ​ማም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ቢያ​ቀ​ር​ቡም ደስ አል​ሰ​ኝ​ባ​ቸ​ውም፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሊያ​መ​ል​ጡት የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ክፉ ነገር በዚህ ሕዝብ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እኔም ይጮ​ኻሉ፤ እኔ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ፍር​ድን ትለይ ዘንድ ለራ​ስህ ማስ​ተ​ዋ​ልን ለመ​ንህ እንጂ ለራ​ስህ ብዙ ዘመ​ና​ትን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ንም፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ህ​ንም ነፍስ ሳት​ለ​ምን ይህን ነገር ለም​ነ​ሃ​ልና፥


የሚ​ለ​ምን ሁሉ ይሰ​ጠ​ዋ​ልና፤ የሚ​ፈ​ል​ግም ያገ​ኛ​ልና፤ ደጅ ለሚ​መ​ታም ይከ​ፈ​ት​ለ​ታ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios