Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 75:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ፍር​ድን ከሰ​ማይ ታሰ​ማ​ለህ። ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በእግዚአብሔር እጅ ጽዋ አለ፤ በሚገባ የተቀመመና ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ ሞልቶበታል፤ ይህን ከውስጡ ወደ ውጭ ገለበጠው፤ የምድር ዐመፀኞችም አተላውን ሳይቀር ይጨልጡታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህንን ያዋርዳል ያንንም ያከብራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 75:8
15 Referencias Cruzadas  

ዐይ​ኖቹ ልጆቹ ሲወጉ ያያሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አያ​ድ​ና​ቸ​ውም።


በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።


በጠ​ላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤ ተስ​ፋ​ዬም ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና መራ​ኸኝ።


አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳ​ደ​ባል? ስም​ህ​ንስ ጠላት ሁል​ጊዜ ያስ​ቈ​ጣ​ዋል?


የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የወይንን ፍለጋ ለሚከተሉስ አይደለምን? ግብዣ ከተደረገ ዘንድ በወይን አትስከሩ፥ ነገር ግን ከደጋግ ሰዎች ጋር በመደማመጥ ተነጋገሩ።


የወ​ይን ጠጅ ለሚ​ጠጡ ኀያ​ላን፥ የሚ​ያ​ሰ​ክ​ረ​ው​ንም መጠጥ ለሚ​ደ​ባ​ልቁ ጽኑ​ዓን ወዮ​ላ​ቸው!


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ የቍ​ጣ​ውን ጽዋ የጠ​ጣሽ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚ​ያ​ን​ገ​ደ​ግ​ድ​ሽን የቍ​ጣ​ውን ጽዋ ጠጥ​ተ​ሻ​ልና፥ ጨል​ጠ​ሽ​ው​ማ​ልና።


ለወ​ገኑ የሚ​ፈ​ርድ አም​ላ​ክሽ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ የሚ​ያ​ን​ገ​ደ​ግ​ድ​ሽን ጽዋ የቍ​ጣ​ዬ​ንም ጽዋ ከእ​ጅሽ ወስ​ጃ​ለሁ፤ ደግ​መ​ሽም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ጠ​ጪ​ውም።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ያል​ተ​በ​ረዘ የዚ​ህን ቍጣ የወ​ይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አን​ተን የም​ሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ አጠ​ጣ​ቸው።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ጽዋ​ውን ወሰ​ድሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እኔን የላ​ከ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ ሁሉ አጠ​ጣ​ኋ​ቸው።


ትጠ​ጪ​ዋ​ለሽ፥ ትጨ​ል​ጪ​ው​ማ​ለሽ፤ በዓ​ላ​ት​ሽ​ንና መባ​ቻ​ዎ​ች​ሽን እሽ​ራ​ለሁ፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሀ ያደ​ር​ጋል፤ ባለ​ጠ​ጋም ያደ​ር​ጋል፤ ያዋ​ር​ዳል፤ ደግ​ሞም ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos