በነጋውም ሙሴ ለሕዝቡ፥ “እናንተ ታላቅ በደል ሠርታችኋል፤ አሁንም አስተሰርይላችሁ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ፤” አላቸው።
ዘሌዋውያን 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም በወይፈኑ ያደርጋል፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት በታረደው ወይፈን እንደ አደረገ እንዲሁ በዚህ ያደርጋል፤ ካህኑም ኀጢአታቸውን ያስተሰርያል፤ ኀጢአቸውም ይሰረይላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኀጢአት መሥዋዕት ባቀረበው ወይፈን ላይ እንዳደረገው ሁሉ፣ በዚህኛውም ወይፈን ያድርግ፤ በዚህም መሠረት ካህኑ ስለ ሕዝቡ ያስተሰርያል፤ እነርሱም ይቅር ይባላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኃጢአት መሥዋዕት በሆነው ወይፈን ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በዚህ ወይፈን ላይ ደግሞ ያደርጋል፤ እርሱም እንዲህ ያደርግበታል፤ ካህኑም ስለ እነርሱ ያስተሰርያል፥ እነርሱም ይቅር ይባላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አፈጻጸሙም ለኃጢአት መሥዋዕት በሚቀርበው ኰርማ ላይ በሚደረገው ዐይነት ይሁን፤ በዚህም ዐይነት ስለ ሕዝቡ ኃጢአት መሥዋዕትን ያቀርባል፤ ሕዝቡም የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በወይፈኑ ያደርጋል፤ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት በታረደው ወይፈን እንዳደረገ እንዲሁ በዚህ ያደርጋል፤ ካህኑም ስለ እነርሱ ያስተሰርያል፥ እነርሱም ይቅር ይባላሉ። |
በነጋውም ሙሴ ለሕዝቡ፥ “እናንተ ታላቅ በደል ሠርታችኋል፤ አሁንም አስተሰርይላችሁ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ፤” አላቸው።
ጠቦት ለማምጣት የሚበቃ ገንዘብ በእጅዋ ባይኖራት ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እርስዋም ትነጻለች።”
በካህኑም እጅ ውስጥ የቀረውን ዘይት ካህኑ በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያደርግበታል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል።
ካህኑም አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስተሰርይለታል።
ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት በእግዚአብሔር ፊት በበደል መሥዋዕት በግ ያስተሰርይለታል፤ የሠራውም ኀጢአት ይቀርለታል።
ወይፈኑንም ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ይወስዱታል፤ የፊተኛውንም ወይፈን እንዳቃጠሉ ያቃጥሉታል፤ የማኅበሩ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና።
ስቡንም ሁሉ እንደ ደኅንነት መሥዋዕት ስብ፥ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። ካህኑም ኀጢአቱን ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
ስቡ ሁሉ ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው የበግ ጠቦት ላይ እንደሚወሰድ ስብዋን ሁሉ ይወስዳሉ፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር በእሳት በተቃጠለው ቍርባን ላይ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል።
ለኀጢአትም መሥዋዕት ከሚታረደው ወይፈን ስብን ሁሉ ይወስዳል፤ ሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
እንደ ሥርዐቱም ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል።
ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል። የተረፈውም እንደ እህሉ ቍርባን ለካህኑ ይሆናል።”
በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢአት ዕዳ ይከፍላል፤ አምስተኛውንም እጅ ይጨምርበታል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
ነውር የሌለበትን በሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣዋል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሳተው ስሕተት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
እግዚአብሔርን ስለ መበደሉና ስለ ሠራው ኀጢአት ከበጎቹ ነውር የሌለባትን እንስት በግ ወይም ከፍየሎች እንስት ፍየል ያመጣል፤ ካህኑም ስለ ኀጢአቱ ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል።
ካህኑም ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ያስተሰርይላቸዋል፤ ባለማወቅ ነበርና ይሰረይላቸዋል፤ እነርሱም ስለ ኀጢአታቸውና ስላለማወቃቸው ቍርባናቸውንና መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ።
ካህኑም ባለማወቅ ስለ በደለው ያስተሰርያል፤ ባለማወቅም በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ስለ ሠራው ሰው ያስተሰርይለታል።
በዚህ ብቻ አይደለም፤ በእርሱ ይቅርታውን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም በእግዚአብሔር ዘንድ እንመካለን እንጂ።
እኛንስ ክርስቶስ ስለ እኛ የኦሪትን መርገም በመሸከሙ ከኦሪት መርገም ዋጅቶናል፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
ስለዚህም የሕዝብን ኀጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።
ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።