እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን አመጣለሁ፥
ዘሌዋውያን 26:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተም ተለይተው የቀሩት ስለ ኀጢአታቸው ይጠፋሉ፤ በአባቶቻቸውም ኀጢአት ደግሞ በጠላቶቻቸው ምድር ይቀልጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ የተረፉት በጠላቶቻቸው ምድር በራሳቸው ኀጢአትና በአባቶቻቸው ኀጢአት ምክንያት መንምነው ያልቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተም መካከል የተረፉት በጠላቶቻቸው ምድር ላይ በኃጢአታቸው ይመነምናሉ፤ በአባቶቻቸውም ኃጢአት ደግሞ እንደ እነርሱ ይመነምናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠላቶቻችሁ ምድር ከሞት ተርፋችሁ የምትቀሩት ጥቂቶቻችሁ፥ በራሳችሁና በቀድሞ አባቶቻችሁ ኃጢአት ምክንያት መንምናችሁ ትቀራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተም ተለይተው የቀሩት በጠላቶቻቸው ምድር ላይ በኃጢአታቸው ይከሳሉ፤ በአባቶቻቸውም ኃጢአት ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይከሳሉ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን አመጣለሁ፥
ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድለናል፤ ስለ ኀጢአታችን እኛና ልጆቻችን ንጉሦቻችን፥ ካህናቶቻችንም ለሰይፍና ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለዕፍረት በአሕዛብ ነገሥታት እጅ ተጣልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊታችን እፍረት እንኖራለን።
ወደ እኔ ብትመለሱ ግን፥ ትእዛዜንም ብትጠብቁ፥ ብታደርጓትም ምንም ከእናንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበተኑ፥ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ለብዙ ሺህ ጽድቅን የሚጠብቅ፥ ቸርነትን የሚያደርግ፥ አበሳንና መተላለፍን፥ ኀጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኀጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው” ሲል አወጀ።
እንዳይነሡም፥ ምድርንም እንዳይወርሱ፥ የዓለሙንም ፊት በጦርነት እንዳይሞሉ በአባቶቻቸው በደል ይገድሉአቸው ዘንድ ልጆችህን አዘጋጅ።”
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።”
ጋሜል። ይሁዳ ስለ ውርደቷና ስለ ባርነቷ ብዛት ተሰደደች፤ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች፤ ዕረፍትም አላገኘችም፤ የሚያሳድዱአት ሁሉ በሚያስጨንቁአት መካከል ያዙዋት።
“እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኀጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን በአደረገ፥ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና በአደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል።
በዚያም የረከሳችሁባትን መንገዳችሁንና ሥራችሁን ሁሉ ታስባላችሁ፤ በፊታችሁም አይታችሁ ስለ ሠራችሁት ክፋታችሁ ሁሉ ታፍራላችሁ።
መጠምጠሚያችሁም በራሳችሁ፥ ጫማችሁም በእግራችሁ ይሆናል፤ ዋይ አትሉም፤ አታለቅሱምም፤ በኀጢአታችሁም ትሰለስላላችሁ፤ ሁላችሁም ጓደኞቻችሁን ታጽናናላችሁ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤልን ቤት፦ እናንተ፦ በደላችንና ኀጢአታችን በላያችን አሉ፤ እኛም ሰልስለንባቸዋል፤ እንዴትስ በሕይወት እንኖራለን? ብላችሁ ተናግራችኋል በላቸው።
ክፉውን መንገዳችሁንና መልካም ያይደለውን ሥራችሁንም ታስባላችሁ፤ ስለ በደላችሁና ስለ ርኵሰታችሁም ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
በዚያ በተማረኩበት በአሕዛብ ዘንድ ከእናንተ የዳኑት ያስቡኛል፤ ለሰሰኑበት፥ ከእኔም ለራቁበት ለልቡናቸው፥ ለሰሰኑ፥ ጣዖትንም ለተከተሉ ለዓይኖቻቸው ማልሁ፤ ጣዖቶቻቸውን ሁሉ እንዳመለኩ መጠን ስለ ሥራቸው ክፋት ፊታቸውን ይነጫሉ።
እግዚአብሔር መዓቱ የራቀ ምሕረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፥ ኀጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኀጢአት እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።
በእነዚያም አሕዛብ መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ አይሆንም፤ በዚያም እግዚአብሔር ተንቀጥቃጭ ልብ ፥ ፈዛዛ ዐይን፥ ደካማም ነፍስ ያመጣብሃል።
“እንዲህም ይሆናል፤ እኔ በፊትህ ያኖርሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረከቱና መርገሙ በወረደብህ ጊዜ፥ አምላክህ እግዚአብሔር በሚበትንህ በዚያ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ሆነህ በልብህ ዐስበው፤
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስለ አልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፊታችሁ እንደሚአጠፋቸው እንደ አሕዛብ ሁሉ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።