ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፤ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
ዘሌዋውያን 26:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመካከላችሁም እመላለሳለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከላችሁ እመላለሳለሁ፤ አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከላችሁም እመላለሳለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፥ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ፤ አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላችሁም እሄዳለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፥ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። |
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፤ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
በውስጥዋ የምትኖርባትን ይህችን ምድር፥ የከነዓንን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ይገዙአት ዘንድ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ በገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
ሄኖክም እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ ሄኖክም ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ።
ከእስራኤል ልጆች ሁሉ ጋር ባለፍሁበት ስፍራ ሁሉ፦ ስለምን ቤትን ከዝግባ እንጨት አልሠራችሁልኝም? ብዬ ሕዝቤን እስራኤልን ይጠብቅ ዘንድ ከእስራኤል ነገድ ላዘዝሁት ለአንዱ በውኑ ተናግሬአለሁን?
በእነርሱ እጠራ ዘንድ፥ አምላክም እሆናቸው ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አምላካቸው እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ደግሞም፥ “እኔ የአባቶችህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን መለሰ።
ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፤ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ከግብፅ ሀገር ከብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁትን፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ” ያልሁትን ቃሌን ስሙ።
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፤ እኔ አምላክ እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።
እንደ ተቀደሱ በጎች፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም በጎች እንዲሁ የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
የእግዚአብሔርን ታቦትስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው? የሕያው እግዚአብሔር ማደሪያዎች እኛ አይደለንምን? እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “እኔ በእነርሱ አድራለሁ፤ በመካከላቸውም እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል።”
አምላክህ እግዚአብሔር ሊያድንህ፥ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈርህ ውስጥ ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን።
አሁን ግን፥ በሰማያት ያለችውን የምትበልጠውን ሀገር ተስፋ ያደርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእነርሱ አያፍርም፤ ተስፋ ያደረጉአትን ሀገር አዘጋጅቶላቸዋልና።
“በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፦