በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
ዘሌዋውያን 24:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሮንና ለልጆቹም ይሁን፤ በእሳት ከተደረገው ከእግዚአብሔር ቍርባን ለዘለዓለም ሥርዐት ለእርሱ ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኅብስቱ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ነው፤ በተቀደሰ ስፍራም ይበሉታል፤ ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው መሥዋዕት እጅግ የተቀደሰ ድርሻቸው ነውና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ለጌታም በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ውስጥ በዘለዓለም ሥርዓት፥ ለእርሱ እጅግ ቅዱስ የሆነ ድርሻ ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የእስራኤል ሕዝብ ዘወትር ሊፈጽሙት የሚገባ የቃል ኪዳን ሥርዓት ነው። ኅብስቱ የአሮንና የልጅ ልጆቹ ድርሻ ይሆናል፤ እነርሱም በተቀደሰ ቦታ ይብሉት፤ እርሱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል ቅዱስ መሥዋዕት ሆኖ ከቀረበ በኋላ ለካህናቱ የተለየ ቋሚ ድርሻ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሮንና ለልጆቹም ይሁን፤ በእሳት ከተደረገው ከእግዚአብሔር ቍርባን በዘላለም ሥርዓት ለእርሱ ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት። |
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን አላቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን የቀረውን የስንዴውን ቍርባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤
“ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና፥ የሕዝቡንም ኀጢአት እንድትሸከሙ፥ በእግዚአብሔርም ፊት እንድታስተሰርዩላቸው ይህን ትበሉ ዘንድ ለእናንተ ሰጥቶታልና ስለ ምን የኀጢአትን መሥዋዕት በቅዱሱ ስፍራ አልበላችሁም?
አባቱ ግብፃዊ የነበረ የእስራኤላዊት ሴት ልጅ በእስራኤል ልጆች መካከል ወጣ፤ የእስራኤላዊቱ ሴት ልጅና አንድ እስራኤላዊ ሰው በሰፈር ውስጥ ተጣሉ፤
ከእርሱም የተረፈውን አሮንና ልጆቹ ይበሉታል፤ ቂጣ ሆኖ በተቀደሰው ስፍራ ይበላል፤ በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ባለው አደባባይ ይበሉታል።
“አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ የሚቃጠለው የመሥዋዕቱ ሕግ ይህ ነው፤ የመሠዊያው እሳት በላዩ እየነደደች እስኪነጋ ትተዉታላችሁ።
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አላቸው፥ “ሥጋውን በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በተቀደሰው ቦታ ቀቅሉ፤ አሮንና ልጆቹ ይብሉት ብሎ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ በዚያ እርሱንና በቅድስናው መሶብ ያለውን እንጀራ ብሉ።
አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።
ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንደ ገባ፥ ከካህናቱም ብቻ በቀር ሊበሉት የማይገባውን የመሥዋዕቱን ኅብስት ወስዶ እንደ በላ፥ አብረውት ለነበሩትም እንደ ሰጣቸው አላነበባችሁምን?
ካህኑ አቤሜሌክም በእርሱ ፋንታ ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ከአለው ኅብስት በቀር ሌላ እንጀራ አልነበረምና የቍርባኑን ኅብስት ሰጠው።