Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 24:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኅብስቱ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ነው፤ በተቀደሰ ስፍራም ይበሉታል፤ ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው መሥዋዕት እጅግ የተቀደሰ ድርሻቸው ነውና።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሱም ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ለጌታም በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ውስጥ በዘለዓለም ሥርዓት፥ ለእርሱ እጅግ ቅዱስ የሆነ ድርሻ ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ይህም የእስራኤል ሕዝብ ዘወትር ሊፈጽሙት የሚገባ የቃል ኪዳን ሥርዓት ነው። ኅብስቱ የአሮንና የልጅ ልጆቹ ድርሻ ይሆናል፤ እነርሱም በተቀደሰ ቦታ ይብሉት፤ እርሱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል ቅዱስ መሥዋዕት ሆኖ ከቀረበ በኋላ ለካህናቱ የተለየ ቋሚ ድርሻ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ይሁን፤ በእ​ሳት ከተ​ደ​ረ​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ለእ​ርሱ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይብ​ሉት።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ለአሮንና ለልጆቹም ይሁን፤ በእሳት ከተደረገው ከእግዚአብሔር ቍርባን በዘላለም ሥርዓት ለእርሱ ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 24:9
17 Referencias Cruzadas  

በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተውጭ ይኸውም ከምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ መብራቶቹን ከምሽት እስከ ንጋት በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።


ሙሴም አሮንንና የተረፉትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው የእህል ቍርባን የቀረውን ወስዳችሁ ቂጣ ጋግሩ፤ እጅግ ቅዱስ ስለ ሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት።


“የኀጢአት መሥዋዕቱን ለምን በተቀደሰው ስፍራ አልበላችሁትም? እጅግ የተቀደሰ ነው፤ በእግዚአብሔር ፊት ስርየት በማስገኘት የሕዝቡን ኀጢአት እንድታስወግዱበት የተሰጣችሁ ነበር፤


እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን ምግብ ይብላ።


እናቱ እስራኤላዊት፣ አባቱ ግብጻዊ የሆነ አንድ ሰው በእስራኤላውያን መካከል ወጣ፤ በሰፈርም ውስጥ ከአንድ እስራኤላዊ ጋራ ተጣሉ።


“ ‘በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ፣ ሥብ ወይም ደም ከቶ አትብሉ፤ ይህ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የተሰጠ የዘላለም ሥርዐት ነው።’ ”


ከዚያም ልብሱን አውልቆ ሌላ ልብስ ይቀይር፤ ዐመዱንም ተሸክሞ ከሰፈር ውጭ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ ወደ ሆነ ስፍራ ይውሰድ።


የተረፈውንም አሮንና ልጆቹ ይብሉት፤ ቂጣውን በተቀደሰው ስፍራ፣ በመገናኛው ድንኳን ቅጥር ግቢ ውስጥ አደባባዩ ላይ ይብሉት።


“አሮንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ስለሚቃጠለው መሥዋዕት አቀራረብ የምትከተለው ሥርዐት ይህ ነው፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት ሌሊቱን ሁሉ እስኪነጋ ድረስ በመሠዊያው ላይ ባለው ማንደጃ ላይ ይቀመጥ፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ሲነድድ ይደር።


ማኅበሩን በሙሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስብ።”


ሙሴም አሮንና ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉት፤ በዚያም፣ ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ተብዬ በታዘዝሁት መሠረት፣ በክህነት መስጫው መሥዋዕት መሶብ ውስጥ ካለው ቂጣ ጋራ ብሉት፤


“እናንተ ግን የእግዚአብሔር ገበታ፣ ‘ርኩስ ነው’ ምግቡም፣ ‘የተናቀ ነው’ በማለት ታቃልላላችሁ።


ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፤ ለካህናት እንጂ ለርሱም ሆነ ዐብረውት ለነበሩት ያልተፈቀደውን ኅብስተ ገጽ በላ።


በሊቀ ካህናቱ በአብያታር ዘመን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ካህናት ብቻ እንዲበሉት የተፈቀደውን ኅብስተ ገጽ ለርሱም ሆነ ዐብረውት ለነበሩትም ሰጣቸው።”


ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ለካህናት ብቻ የተፈቀደውን ኅብስተ ገጽ ወስዶ በላ፤ ዐብረውት ለነበሩትም ሰጣቸው።”


ስለዚህ ካህኑ የተቀደሰውን እንጀራ ለዳዊት ሰጠው፤ ከእግዚአብሔር ፊት ተነሥቶ በትኵስ እንጀራ ከተተካው ከገጸ ኅብስቱ በቀር በዚያ ሌላ እንጀራ አልነበረምና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos