La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 23:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ጀ​ራ​ው​ንም፥ የተ​ጠ​በ​ሰ​ው​ንም እሸት፥ ለም​ለ​ሙ​ንም እሸት የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቍር​ባን እስ​ከ​ም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት እስ​ከ​ዚህ ቀን ድረስ አት​ብሉ። ይህ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስጦታውን ለአምላካችሁ እስከምታቀርቡበት እስከዚያ ቀን ድረስ፣ እንጀራም ቢሆን ቈሎ ወይም እሸት አትብሉ፤ ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዐት ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአምላካችሁን ቁርባን እስከምታመጡበት እስከዚህ ቀን ድረስ እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህንንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ከማቅረባችሁ በፊት ከአዲሱ እህል ጥሬውን ወይም የተቈላውን ወይም እንጀራ ጋግራችሁ አትብሉ። ይህም ድንጋጌ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በልጅ ልጆቻችሁ ተጠብቆ ይኑር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት የአምላካችሁን ቍርባን እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 23:14
15 Referencias Cruzadas  

የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ሰን​በ​ት​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ሃ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝ​ንና ሥር​ዐ​ትን፥ ሕግ​ንም በባ​ሪ​ያህ በሙሴ እጅ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።


እነ​ርሱ ተሰ​ነ​ካ​ክ​ለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነ​ሣን፥ ጸን​ተ​ንም ቆምን።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን የም​ድ​ር​ህን ፍሬ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትወ​ስ​ዳ​ለህ። ጠቦ​ቱን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሥር​ዐት ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ታስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።”


“ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው እህ​ልህ መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ቀ​ርብ በእ​ሳት የተ​ጠ​በ​ሰና የተ​ፈ​ተገ የእ​ህል እሸት ታቀ​ር​ባ​ለህ።


ሥራ ሁሉ አታ​ድ​ር​ጉ​ባት፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ነው።


በየ​ዓ​መቱ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ይህን በዓል ታደ​ርጉ ዘንድ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”


አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ ዐስብ፤ ይህ​ንም ሥር​ዐት ጠብቅ፤ አድ​ር​ገ​ውም።