Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 23:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የስ​ን​ዴም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ይሁን፤ የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን የወ​ይን ጠጅ የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚህም ጋራ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን ሁለት ዐሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ለእህል ቍርባን፣ አንድ አራተኛ የሂን መስፈሪያ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን አቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእህልም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ይሁን፤ ለመጠጥም ቁርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የሆነ የወይን ጠጅ ይቅረብ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከእርሱም ጋር በወይራ ዘይት የተለወሰ ሁለት ኪሎ የላመ ዱቄት የምግብ መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤ ይህም መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል፤ ከዚህም ጋር አንድ ሊትር የሚሆን የወይን ጠጅ ስጦታ ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ለእሳት ቍርባን ይሁን፤ የመጠጡም ቍርባን የወይን ጠጅ የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 23:13
15 Referencias Cruzadas  

ብር​ጉ​ድም አም​ስት መቶ ሰቅል እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወ​ይራ ዘይ​ትም አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


ሌላም ዕጣን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አታ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም፤ የመ​ጠ​ጥም ቍር​ባን አታ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም።


ውኃ​ው​ንም በልክ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ከስ​ድ​ስት እጅ አንድ እጅ ትጠ​ጣ​ለህ፤ በየ​ጊ​ዜው ትጠ​ጣ​ዋ​ለህ።


ለአ​ን​ድም ወይ​ፈን አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ን​ድም አውራ በግ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ን​ድም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ለእ​ህል ቍር​ባን ያቅ​ርብ።


ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ህ​ልን ቍር​ባን፥ በኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ስድ​ስ​ተኛ እጅ የስ​ንዴ ዱቄ​ትን፤ በየ​ማ​ለ​ዳው ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ይህ የሚ​ደ​ረግ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ሥር​ዐት ነው።


መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት ቀር​ቶ​አ​ልና እና​ንተ ካህ​ናት! ማቅ ታጥ​ቃ​ችሁ አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የመ​ሠ​ውያ አገ​ል​ጋ​ዮች! ዋይ በሉ፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።


መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተወ​ግ​ዶ​አል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሠ​ውያ የም​ታ​ገ​ለ​ግሉ ካህ​ናቱ፥ አል​ቅሱ።


የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?


“በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ዓመት የሞ​ላ​ቸ​ውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ት​ንም አን​ዲት የዓ​መት እን​ስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህ​ልም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይ​ትም ይወ​ስ​ዳል።


ነዶ​ው​ንም ባቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።


“እር​ሱን በቀ​ባ​ህ​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ መባ ይህ ነው። የኢፍ መስ​ፈ​ርያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካ​ሙን ዱቄት እኩ​ሌ​ታ​ውን በጥ​ዋት፥ እኩ​ሌ​ታ​ው​ንም በማታ ለዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባሉ።


በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ፥ በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ይህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos