Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 19:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነ​ርሱ ተሰ​ነ​ካ​ክ​ለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነ​ሣን፥ ጸን​ተ​ንም ቆምን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ዐይንን ያበራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የጌታ ሕግ ፍጹም ነው፥ ነፍስን ይመልሳል፥ የጌታ ምስክር የታመነ ነው፥ የዋሆችን ጠቢባን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የእግዚአብሔር ሕግ ትክክል ነው፤ ለልብ ደስታን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ለዐይን ብርሃንን ይሰጣል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 19:8
44 Referencias Cruzadas  

አባ​ትህ አብ​ር​ሃም ቃሌን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ፍር​ዴን፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ሕጌ​ንም ጠብ​ቆ​አ​ልና።”


የጻ​ፈ​ላ​ች​ሁ​ንም ሥር​ዐ​ትና ፍርድ፥ ሕግና ትእ​ዛ​ዝም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አት​ፍሩ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ የተ​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃል አስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ልና ሊበ​ሉና ሊጠጡ፥ እድል ፈን​ታም ሊልኩ፥ ደስ​ታም ሊያ​ደ​ርጉ ሄዱ።


ወደ ሲናም ተራራ ወረ​ድህ፤ ከሰ​ማ​ይም ተና​ገ​ር​ሃ​ቸው፤ ቅኑን ፍር​ድና እው​ነ​ቱን ሕግ፥ መል​ካ​ሙ​ንም ሥር​ዐ​ትና ትእ​ዛዝ ሰጠ​ሃ​ቸው፤


ለእ​ነ​ር​ሱም ኪዳ​ኑን አሰበ፥ እንደ ምሕ​ረ​ቱም ብዛት አዘ​ነ​ላ​ቸው።


ከክፉ ነገ​ርም አይ​ፈ​ራም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ታ​መን ልቡ የጸና ነው።


የረ​ዳ​ኝን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስምም እዘ​ም​ራ​ለሁ።


ሁሉ ተስ​ተ​ካ​ክሎ በአ​ን​ድ​ነት ዐመፀ፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ሠ​ራት የለም፤ አን​ድም እንኳ የለም።


የበ​ደ​ልን ነገር በእኔ አወጡ። የተኛ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ነ​ቃ​ምን?


አቤቱ፥ ሕዝ​ብ​ህን አዋ​ረዱ፥ ርስ​ት​ህ​ንም አሠ​ቃዩ።


ነገ​ርም ቢኖ​ራ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤ በዚ​ህና በዚያ ሰውም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ትና ሕግ አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።


እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤


ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፥ ትምህርትና ተግሣጽም የሕይወት መንገድ ነውና፥


በቸ​ር​ነ​ትህ የሚ​ታ​ገሡ መን​ገ​ድ​ህ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ይገ​ና​ኙ​ሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈ​ጣህ፤ እኛም ኀጢ​አት ሠራን፤ ስለ​ዚ​ህም ተሳ​ሳ​ትን።


ቃልህ ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ እኔም በል​ች​ዋ​ለሁ፤ አቤቱ! የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ ሆይ! ቃል​ህን የከዱ ሰዎ​ችን አጥ​ፋ​ቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠ​ር​ት​ዋ​ልና፥ ቃልህ ሐሤ​ትና የልብ ደስታ ሆነኝ።


መን​ፈ​ሴ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ በት​እ​ዛ​ዜም እን​ድ​ት​ሄዱ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ዴ​ንም ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ ታደ​ር​ጉ​ት​ማ​ላ​ችሁ።


ከኦ​ሪት የተ​ነሣ ኀጢ​አት ስለ ታወ​ቀች ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሥር​ዐት በመ​ፈ​ጸም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አይ​ጸ​ድ​ቅም።


በል​ቡ​ናዬ ውስጥ ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መል​ካም ነው።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ኦሪት ኀጢ​አት ናትን? አይ​ደ​ለ​ችም፤ ነገር ግን ኦሪት ባት​ሠራ ኀጢ​አ​ትን ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር፤ ኦሪት፥ “አት​መኝ” ባትል ኖሮም ምኞ​ትን ፈጽሞ ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር።


እኔስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ሆኜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሕግ እኖር ዘንድ ከቀ​ደ​መው ሕግ ተለ​የሁ።


እን​ግ​ዲህ ኦሪት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ልት​ከ​ለ​ክል መጣ​ችን? አይ​ደ​ለም፤ ማዳን የሚ​ቻ​ለው ሕግ ተሠ​ርቶ ቢሆ​ንማ፥ በእ​ው​ነት በዚያ ሕግ ጽድቅ በተ​ገኘ ነበር።


አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ህም ያሉ መጻ​ተ​ኛና ድሃ-አደግ፥ መበ​ለ​ትም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በሚ​መ​ር​ጠው ስፍራ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


አን​ተም፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለ ሌዋ​ዊና መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግና መበ​ለ​ትም በበ​ዓ​ልህ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos