እነርሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
ሰቈቃወ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ የሆነብንን ዐስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን ዐስብ፤ ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤ ውርደታችንንም ተመልከት! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ። |
እነርሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
አምላካችን ሆይ፥ ተንቀናልና ስማ፤ ስድባቸውን በራሳቸው ላይ መልስባቸው፤ በምርኮ ሀገር ለብዝበዛ አሳልፈህ ስጣቸው።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጠባቂዎችሽን በቅጥርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁሜአለሁ፤ እግዚአብሔርን የሚያስቡ ከቶ ዝም አይሉም፤
አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤ ከሚያሳድዱኝም አድነኝ እንጂ፥ አትታገሣቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደቡኝ አስብ።
ስድባችንን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም ወደ ቤተ መቅደሳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ከድኖታል።
ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እንጀራ አጥተው ያለቅሳሉ፤ ሰውነታቸውን ለማበርታት ፍላጎታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፤ አቤቱ! ተጐሳቍያለሁና እይ፤ ተመልከትም።
ሬስ። አቤቱ! ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፤ መራራ ኀዘን አዝኛለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ አመከነችኝ፤ በቤትም ሞት አለ።
ጤት። ግዳጅዋ ከእግርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻሜዋን አላሰበችም፤ ከባድ ሸክምን ተሸከመች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት።
ሳምኬት። መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፦ “በውኑ የምድር ሁሉ ደስታ፥ አክሊልና ክብር የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ።
ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመልከት ማንን እንዲህ ቃረምህ? በውኑ ሴቶች የማኅፀናቸውን ፍሬ፥ ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?