ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ፥ ሰድቦሻልና ንቆሻልምና፥ የኢየሩሳሌም ልጅ፥ በአንቺ ላይ ራሱን ነቅንቋልና እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦
ሰቈቃወ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዋው። ከጽዮን ሴት ልጅ ውበት ሁሉ ተወስዶአል፤ አለቆችዋ መሰማሪያ እንደማያገኙ አውራ በጎች ሆኑ፤ ከሚያባርሩአቸው ፊት ተዳክመው ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተለይቷታል፤ መሳፍንቷ፣ መሰማሪያ እንዳጣ ዋሊያ ናቸው፤ በአሳዳጆቻቸው ፊት፣ በድካም ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዋው። ከጽዮን ሴት ልጅ ውበትዋ ሁሉ ወጥቶአል፥ አለቆችዋ ማሰማርያ እንደማያገኙ ዋላዎች ሆኑ፥ ከሚያባርሩአቸው ፊት ተዳክመው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሩሳሌም ክብር ሁሉ ጠፍቶአል፤ መሪዎችዋ መሰማሪያ እንዳጡ ዋልያዎች ናቸው፤ አሳዳጆቻቸው ሲያባርሩአቸው ጒልበታቸው እስኪዝል ድረስ ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዋው። ከጽዮን ሴት ልጅ ውበትዋ ሁሉ ወጥቶአል፥ አለቆችዋ ማሰማርያ እንደማያገኙ ዋላዎች ሆኑ፥ ከሚያባርሩአቸው ፊት ተዳክመው ሄዱ። |
ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ፥ ሰድቦሻልና ንቆሻልምና፥ የኢየሩሳሌም ልጅ፥ በአንቺ ላይ ራሱን ነቅንቋልና እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦
ከተማዪቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ በሁለት ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ሸሹ፤ ከለዳውያንም በከተማዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ምድረ በዳ በሚወስደውም መንገድ ሄዱ።
የከለዳውያንም ሠራዊት ንጉሡን ተከተሉ፤ በኢያሪኮም በኩል ባለው ሜዳ ያዙት፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ተለይተው ተበትነው ነበር።
ፍርድ መልቶባት የነበረ የታመነችይቱ የጽዮን ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፤ አሁን ግን ወንበዴዎችና ነፍሰ ገዳዮች አሉባት።
እግዚአብሔርም ይመጣል፤ በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ቦታ ሁሉ፥ በዙሪያውም ላይ ደመና በቀን እንደ ጢስ፥ በሌሊትም እንደሚቃጠል የእሳት ብርሃን ይጋርዳል፤ በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ላስማረክኋቸው ምርኮኞች ሁሉ እንዲህ ይላል፦
ከኀይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መሽከርከር፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው አይመለሱም።
የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው፤ ወደ ባቢሎንም ወሰደው፤ እስኪሞትም ድረስ በግዞት ቤት አኖረው።
የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፥ በእሳት አቃጠለ።
ለእስራኤል ቤት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኀይላችሁን ትምክሕት፥ የዐይናችሁን አምሮት፥ የነፍሳችሁንም ምኞት፥ መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ኀይላቸውን፥ የተመኩበትንም ደስታ፥ የዐይናቸውንም አምሮት፥ የነፍሳቸውንም ምኞት፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥
“እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፤ በሰባት መንገድም ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ የተበተንህ ትሆናለህ።
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።