ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በግዞት አኑሩት፤ የመከራም እንጀራ መግቡት፤ የመከራም ውኃ አጠጡት በሉአቸው” አለ።
ዮሐንስ 9:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተነጋገረው እናውቃለን፤ ይህን ግን ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ መጣ እንኳ አናውቅም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እኛ እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደሆነ አናውቅም፤” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳነጋገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ ሆነ አናውቅም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እኛ እናውቃለን፥ ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም” አሉት። |
ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በግዞት አኑሩት፤ የመከራም እንጀራ መግቡት፤ የመከራም ውኃ አጠጡት በሉአቸው” አለ።
ኢዩም ወደ ጌታው ብላቴኖች ወጣ፤ እነርሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እርሱም፥ “ሰውዬው ፌዝ እንደሚናገር አታውቁምን?” አላቸው።
እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄሣር ግብር እንዳይሰጡ ሲከለክልና ሕዝቡን ሲያሳምፅ፥ ራሱንም የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስን ሲያደርግ አገኘነው።”
ጌታችን ኢየሱስም በመቅደስ ሲያስተምር ቃሉን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔ ራሴ የመጣሁ አይደለሁም፤ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ አለ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ ስለራሴ ብመሰክርም ምስክርነቴ እውነት ነው፤ ከየት እንደመጣሁ፥ ወዴት እንደምሄድም አውቃለሁና፤ እናንተ ግን ከየት እንደ መጣሁ ወዴት እንደምሄድም አታውቁም።
ከፈሪሳውያንም አንዳንዶች፥ “ይህ ሰው ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ሰንበትን አያከብርምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢኣተኛ ሰው እንዲህ ያለ ተአምራት ማድረግ እንዴት ይችላል?” አሉ፤ እርስ በርሳቸውም ተለያዩ።
ዕውር የነበረውንም ሰው ዳግመኛ ጠርተው፥ “ሂድ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርብ፤ ይህ ሰው ኀጢኣተኛ እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን” አሉት።
ያም ሰው መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ከወዴት እንደ ሆነ፥ አታውቁትምና ይህ እጅግ ድንቅ ነው፤ ነገር ግን ዐይኖችን አበራልኝ።
ከጳውሎስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕይወት ሊኖር አይገባውምና እንዲህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው” እያሉ ጮሁ።
እግዚአብሔርም አዳነኝና ለታላቁም፥ ለታናሹም እየመሰከርሁ እስከ ዛሬ ደረስሁ፤ ይደረግ ዘንድ ካለው፥ ነቢያት ከተናገሩት፥ ሙሴም ከተናገረው ሌላ ያስተማርሁት የለም።
“በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ማን አድርጎሃል? ብለው የካዱትን ያን ሙሴን በቍጥቋጦው መካከል በታየው በመልአኩ እጅ እርሱን መልእክተኛና አዳኝ አድርጎ እግዚአብሔር ላከው።