Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 7:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ነገር ግን ይህን ከየት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜስ ከወ​ዴት እንደ ሆነ ማንም አያ​ው​ቅም”።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ይህ ሰው ግን ከየት እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን፤ ክርስቶስ ሲመጣ እኮ ከየት እንደ ሆነ ማንም አያውቅም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ሆኖም ይህ ሰው ከወዴት እንደሆነ አውቀናል፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደሆነ ማንም አያውቅም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ሆኖም ይህ ሰው ከወዴት እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን፤ መሲሕ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደ ሆነ የሚያውቅ ማንም የለም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ነገር ግን ይህን ከወዴት እንደ ሆነ አውቀናል፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደ ሆነ ማንም አያውቅም።”

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 7:27
14 Referencias Cruzadas  

አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እንደ ተነ​ጋ​ገ​ረው እና​ው​ቃ​ለን፤ ይህን ግን ከወ​ዴት እንደ ሆነ አና​ው​ቅም።”


“እኛ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን የም​ና​ው​ቃ​ቸው ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢየ​ሱስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወረ​ድሁ ይለ​ናል?” አሉ።


አለ​ቃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ውስጥ ይሾ​ማል፤ ገዢ​አ​ቸ​ውም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይወ​ጣል፤ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔ ይመ​ለስ ዘንድ ልብ የሰ​ጠው ማን ነው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።


ሁሉም የን​ግ​ግ​ሩን መከ​ና​ወን መሰ​ከ​ሩ​ለት፤ የአ​ን​ደ​በ​ቱ​ንም ቅል​ጥ​ፍና እያ​ደ​ነቁ፥ “ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይሉ ነበር።


ከእ​ሴይ ሥር በትር ትወ​ጣ​ለች፤ አበ​ባም ከግ​ንዱ ይወ​ጣል።


“እነሆ ለዳ​ዊት የጽ​ድቅ ቍጥ​ቋጥ የማ​ስ​ነ​ሣ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ ያስ​ባል፤ በም​ድ​ርም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ያደ​ር​ጋል።


በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዶ​አ​ልና ትው​ል​ዱን ማን ይና​ገ​ራል?”


አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ ሳይ​ማር መጽ​ሐ​ፍን እን​ዴት ያው​ቃል?” እያሉ ትም​ህ​ር​ቱን አደ​ነቁ።


በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዷ​ልና ልደ​ቱን ማን ይና​ገ​ራል? ስለ ሕዝቤ ኀጢ​አት ለሞት ደረሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios