ዮሐንስ 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፋሲካ በዓል አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓለም ያሉትን የወደዳቸውን ወገኖቹን ፈጽሞ ወደዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጊዜው ልክ ከፋሲካ በዓል በፊት ነበረ፤ ኢየሱስም ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዐወቀ። በዓለም የነበሩትን፣ የራሱ የሆኑትን ወደዳቸው፤ በፍጹም ፍቅሩም ወደዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ጊዜው ከአይሁድ ፋሲካ በዓል በፊት ነበር፤ ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት መድረሱን ዐወቀ። በዚህ በዓለም ያሉትን የራሱን ወገኖች ወዶአቸው ነበር፤ እስከ መጨረሻም ወደዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው። |
እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፥ “በዘለዓለም ፍቅር ወድጄሃለሁ፤ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁህ።
ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።
ዘወትርም ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስ ስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው፤ የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው።”
የአይሁድም የፋሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም ከበዓሉ አስቀድሞ ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከየሀገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ነበር።
ሙዳየ ምጽዋቱ በይሁዳ ዘንድ ነበረና፥ ለበዓል የምንሻውን ወይም ለነዳያን የምንሰጠውን ግዛ ያለው የመሰላቸው ነበሩ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ባወቀ ጊዜ፥
“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
እኔ እንደምሄድ ወደ እናንተም እንደምመለስ የነገርኋችሁን ሰምታችኋል፤ ብትወዱኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበልጠኛልና።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር ተናግሮ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አነሣና እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአልና ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤
እኔን የወደድህበት ፍቅር በእነርሱ ይኖር ዘንድ፥ እኔም በእነርሱ እኖር ዘንድ ስምህን ነገርኋቸው፤ ደግሞም እነግራቸዋለሁ፤”
ጌታችን ኢየሱስም በቤተ መቅደስ ሲያስተምራቸው በሙዳየ ምጽዋት አጠገብ ይህን ተናገራቸው፤ ነገር ግን አልያዙትም፤ ጊዜው ገና አልደረሰም ነበርና።
ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፤ እኛም የምንደፍርበትን፥ የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።