Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 17:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እኔን የወ​ደ​ድ​ህ​በት ፍቅር በእ​ነ​ርሱ ይኖር ዘንድ፥ እኔም በእ​ነ​ርሱ እኖር ዘንድ ስም​ህን ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ደግ​ሞም እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ለእኔ ያለህ ፍቅር በእነርሱ እንዲሆን፣ እኔም በእነርሱ እንድሆን፣ ስምህን እንዲያወቁ አድርጌአለሁ፤ እንዲያውቁትም አደርጋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን፥ እኔም በእነርሱ እንድሆን፥ ስምህን አስታወቅኋቸው፤ አስታውቃቸውማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 አንተ እኔን የወደድክበት ፍቅር በእነርሱ ላይ እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን እነርሱ አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ ደግሞም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እኔንም የወደድህበት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህም አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ።”

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 17:26
28 Referencias Cruzadas  

እኔ በእ​ነ​ርሱ እኖ​ራ​ለሁ፤ አን​ተም በእኔ፤ በአ​ንድ ፍጹ​ማን ይሆኑ ዘንድ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸ​ኝና እንደ ወደ​ድ​ኸኝ እኔም እነ​ር​ሱን እንደ ወደ​ድ​ኋ​ቸው።


“ከዓ​ለም ለይ​ተህ ለሰ​ጠ​ኸኝ ሰዎች ስም​ህን ገለ​ጥሁ፤ ያንተ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለእኔ ሰጥ​ተ​ኸ​ኛል፤ ቃል​ህ​ንም ጠበቁ።


አብ እንደ ወደ​ደኝ እን​ዲሁ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ፤ በፍ​ቅ​ሬም ኑሩ።


“ስም​ህን ለወ​ን​ድ​ሞች እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በማ​ኅ​በር መካ​ከ​ልም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ” አለ።


እን​ግ​ዲህ ወዲህ ባሮች አል​ላ​ች​ሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና፤ እና​ን​ተን ግን ወዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ባቴ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ሁሉ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ፥ አብም በእኔ እን​ዳለ፥ እና​ን​ተም በእኔ፥ እኔም በእ​ና​ንተ እን​ዳ​ለሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእ​ና​ንተ፤ ቅር​ን​ጫፍ በወ​ይኑ ግንድ ከአ​ል​ኖረ ብቻ​ውን ሊያ​ፈራ እን​ደ​ማ​ይ​ችል እና​ን​ተም እን​ዲሁ በእኔ ካል​ኖ​ራ​ችሁ ፍሬ ማፍ​ራት አት​ች​ሉም።


ይህም ምሥ​ጢር ታላቅ ነው፤ እኔም ይህ​ንኑ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስና ስለ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያኑ እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።


እኛ የአ​ካሉ ሕዋ​ሳት ነንና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አለው፥ “የሚ​ወ​ደኝ ቃሌን ይጠ​ብ​ቃል፤ አባ​ቴም ይወ​ደ​ዋል፤ ወደ እር​ሱም መጥ​ተን በእ​ርሱ ዘንድ ማደ​ሪያ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


እኔ ለራሴ ክብ​ርን አል​ሻም፤ የሚሻ፥ የሚ​ፈ​ር​ድም አለ።


ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን።


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።


በእ​ርሱ ዘንድ አይ​ሁ​ዳዊ፥ ግሪ​ካ​ዊም፥ የተ​ገ​ዘረ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም፥ አረ​መ​ኔም፥ ባላ​ገ​ርም፥ ቤተ ሰብ​እና አሳ​ዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክር​ስ​ቶስ ለሁሉ በሁ​ሉም ዘንድ ነው።


እና​ን​ተም በእ​ርሱ ፍጹ​ማን ሁኑ፤ እርሱ ለአ​ለ​ቅ​ነት ሁሉና ለሥ​ል​ጣን ሁሉ ራስ ነውና።


ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ምክር የክ​ብር ባለ​ጸ​ግ​ነት በአ​ሕ​ዛብ ላይ እን​ዲ​ገ​ል​ጽ​ላ​ቸው ለፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸው ለቅ​ዱ​ሳን ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፤ የም​ን​ከ​ብ​ር​በት አለ​ኝ​ታ​ችን በእ​ና​ንተ አድሮ ያለ ክር​ስ​ቶስ ነውና።


በል​ባ​ችሁ ውስጥ በፍ​ቅር ሥር መሠ​ረ​ታ​ችሁ የጸና ሲሆን ክር​ስ​ቶስ በሃ​ይ​ማ​ኖት በሰው ውስጥ ያድ​ራ​ልና።


በሚ​ወ​ደው ልጁ የሰ​ጠን የጸ​ጋው ክብር ይመ​ሰ​ገን ዘንድ።


ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋርም ተሰ​ቀ​ልሁ፤ ሕይ​ወ​ቴም አለ​ቀች፤ ነገር ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወት አለሁ፤ ዛሬም በሥ​ጋዬ የም​ኖ​ረ​ውን ኑሮ የወ​ደ​ደ​ኝን ስለ እኔም ራሱን አሳ​ልፎ የሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ በማ​መን እኖ​ራ​ለሁ።


አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአ​ካል ክፍ​ሎ​ችም እንደ አሉ​በት፥ ነገር ግን የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ብዙ​ዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ ክር​ስ​ቶስ ደግሞ እን​ዲሁ ነው፤


እና​ን​ተም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ርሱ ናችሁ፤ በእ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ጽድ​ቅን፥ ቅድ​ስ​ና​ንና ቤዛ​ነ​ትን አገ​ኘን።


ክር​ስ​ቶስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ግን ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ከኀ​ጢ​አት ሥራ ለዩ፤ መን​ፈ​ሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ ሥራ ሕያው አድ​ርጉ።


ሥጋ​ዬን የሚ​በላ፥ ደሜ​ንም የሚ​ጠጣ በእኔ ይኖ​ራል፤ እኔም በእ​ርሱ እኖ​ራ​ለሁ።


የሰ​ጠ​ኽ​ኝን ቃል ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ተቀ​ብ​ለው ከአ​ንተ እንደ ወጣሁ በእ​ው​ነት ዐወቁ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ አመኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios