Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በዚች ጽድቅ እስከ መጨ​ረሻ የቀ​ደ​መ​ውን ሥር​ዐ​ታ​ች​ንን አጽ​ን​ተን ከጠ​በ​ቅን ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ሁነ​ና​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በመጀመሪያ የነበረንን እምነት እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንይዝ ከክርስቶስ ጋራ ተካፋዮች እንሆናለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በመጀመሪያ የነበረንን እምነታችንን እስከ መጨረሻ አጽንተን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ወራሾች እንሆናለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 3:14
17 Referencias Cruzadas  

ክር​ስ​ቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታ​መነ ነው፤ እኛም የም​ን​ደ​ፍ​ር​በ​ትን፥ የም​ን​መ​ካ​በ​ት​ንም ተስፋ እስከ መጨ​ረ​ሻው አጽ​ን​ተን ብን​ጠ​ብቅ ቤቱ ነን።


ነገር ግን ሁላ​ች​ሁም በዚች ተስ​ፋ​ችሁ እን​ዲሁ ትጋ​ታ​ች​ሁን እስከ መጨ​ረ​ሻው ታሳዩ ዘንድ እን​ወ​ዳ​ለን።


ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።


እነ​ርሱ መል​ካም ሆኖ እንደ ታያ​ቸው ለጥ​ቂት ቀን ይቀ​ጡ​ናል፤ እርሱ ግን ከቅ​ድ​ስ​ናው እን​ድ​ን​ካ​ፈል ለጥ​ቅ​ማ​ችን ይቀ​ጣ​ናል።


ነገር ግን አንድ ጊዜ ብር​ሃን የበ​ራ​ላ​ቸ​ውን፥ ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም ስጦታ የቀ​መ​ሱ​ትን፥ ከመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ተካ​ፋ​ዮች ሆነው የነ​በ​ሩ​ትን፥


አሕ​ዛ​ብን ወራ​ሾ​ቹና አካሉ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ፥ በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነው ተስፋ አንድ ይሆኑ ዘንድ።


አሁ​ንም ከሰ​ማ​ያዊ ጥሪ ተካ​ፋ​ዮች የሆ​ና​ችሁ ቅዱ​ሳን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ንን ሐዋ​ር​ያና ሊቀ ካህ​ናት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ተመ​ል​ከቱ።


ከቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ አን​ዳ​ን​ዶቹ ቢሰ​በሩ የዱር ወይራ የሆ​ንህ አን​ተን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ተከሉ፤ የእ​ነ​ር​ሱ​ንም ሥር​ነት አገ​ኘህ፤ እንደ እነ​ር​ሱም ዘይት ሆንኽ።


ኅብ​ስቱ አንድ እንደ ሆነ እን​ዲሁ እኛም ብዙ​ዎች ስን​ሆን አንድ አካል ነን፤ ሁላ​ችን ከአ​ንድ ኅብ​ስት እን​ቀ​በ​ላ​ለ​ንና።


እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።


እና​ን​ተም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ርሱ ናችሁ፤ በእ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ጽድ​ቅን፥ ቅድ​ስ​ና​ንና ቤዛ​ነ​ትን አገ​ኘን።


እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤


የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።


በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት አን​ድ​ነት ይኖ​ረኝ ዘንድ ስለ ወን​ጌል ትም​ህ​ርት ሁሉን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ እሰ​ጣት ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች ማንም አያ​ይም፥


እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርኅ​ራ​ኄ​ው​ንና ጭካ​ኔ​ውን አስ​ተ​ውል፤ የወ​ደ​ቁ​ትን ቀጣ​ቸው፤ አን​ተን ግን ይቅር እን​ዳ​ለህ ብት​ኖር ማረህ፤ ያለ​ዚያ ግን አን​ተም ትቈ​ረ​ጣ​ለህ።


እም​ነ​ትስ ተስፋ ስለ​ም​ና​ደ​ር​ገው ነገር የም​ታ​ረ​ጋ​ግጥ፥ የማ​ና​የ​ው​ንም ነገር የም​ታ​ስ​ረዳ ናት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios