La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም ባሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚ​ህች ክፉ ትው​ልድ የተ​ረፉ ቅሬ​ቶች ሁሉ፥ ከሕ​ይ​ወት ይልቅ ሞትን ይመ​ር​ጣሉ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ሁሉ፣ ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፤ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚህም ክፉ ወገን የቀሩትን ትሩፋን ሁሉ፥ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም ክፉ ትውልድ የተረፉትና እኔ በበተንኳቸው ቦታ የሚኖሩትም ሕዝብ ከመኖር ይልቅ መሞትን ይመርጣሉ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚህች ክፉ ወገን የተረፉ ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 8:3
22 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ።


የሕ​ዝ​ቤን ቅሬታ ከበ​ተ​ን​ኋ​ቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸው ሰብ​ስቤ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይበ​ዛሉ፤ ይባ​ዛ​ሉም።


ነገር ግን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ዘር ከሰ​ሜን ሀገ​ርና ካሳ​ደ​ዷ​ቸ​ውም ሀገር ሁሉ ያወ​ጣና የመራ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን!” ይባ​ላል፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም መልሶ ያኖ​ራ​ቸ​ዋል።


እገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ምር​ኮ​አ​ች​ሁ​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ዘንድ እና​ን​ተ​ንም ከበ​ተ​ን​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እና​ን​ተ​ንም ለም​ርኮ ወዳ​ፈ​ለ​ስ​ሁ​በት ስፍራ እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።


እርሱ፦ ምር​ኮው የረ​ዘመ ነውና ቤት ሠር​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ አታ​ክ​ል​ትም ተክ​ላ​ችሁ ፍሬ​ዋን ብሉ ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢ​ሎን ልኮ​አ​ልና።”


አይ​ሁ​ድም ሁሉ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​በት ስፍራ ሁሉ ተመ​ለሱ፤ ወደ ይሁ​ዳም ሀገር ጎዶ​ል​ያስ ወዳ​ለ​በት ወደ መሴፋ መጡ፤ ወይ​ን​ንና የበ​ጋን ፍሬ፥ ዘይ​ት​ንም እጅግ ብዙ አከ​ማቹ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ያመ​ጣ​ሁ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ከክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ እነሆ ዛሬ ባድማ ሆነ​ዋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸ​ውም የለም።


ስለ​ዚህ መዓ​ቴና መቅ​ሠ​ፍቴ ወረደ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ነደደ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ጠፍና ባድማ ሆኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰው ወይ​ንን እን​ደ​ሚ​ቃ​ርም፥ እን​ዲሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል የቀ​ሩ​ትን ይቃ​ር​ሙ​አ​ቸ​ዋል፤ እጅ​ህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እን​ቅብ ዘርጋ።


እና​ን​ተ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ትም ሁሉ ሰይፍ ታጠ​ፋ​ች​ኋ​ለች፤ ምድ​ራ​ች​ሁም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁም ባድማ ይሆ​ናሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ን​ተና ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ሁት ወገን ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ይህን ቃል ስሙ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦


አሁ​ንም አቤቱ! ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና እባ​ክህ! ነፍ​ሴን ከእኔ ውሰድ።”


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እኔ በፊ​ትህ ያኖ​ር​ሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረ​ከ​ቱና መር​ገሙ በወ​ረ​ደ​ብህ ጊዜ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​በ​ት​ንህ በዚያ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል ሆነህ በል​ብህ ዐስ​በው፤


መበ​ተ​ን​ህም እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢሆን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል፤ ከዚ​ያም ያመ​ጣ​ሃል።


ተራራዎችንና ዐለቶችንም “በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤


በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ አያገኙትምም፤ ሊሞቱም ይመኛሉ፤ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።