Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮናስ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አሁ​ንም አቤቱ! ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና እባ​ክህ! ነፍ​ሴን ከእኔ ውሰድ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ውሰድ፤ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ከሕይወት ሞት ይሻላልና፥ እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አሁንም ጌታ ሆይ! እባክህ ግደለኝ፤ ከመኖር ይልቅ መሞት ይሻለኛል።”

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 4:3
14 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ።


ከመ​ል​ካም ሽቱ መል​ካም ስም፥ ከመ​ወ​ለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻ​ላል።


በመ​ን​ፈ​ስህ ለቍጣ ችኩል አት​ሁን፥ ቍጣ በሰ​ነ​ፎች ብብት ያር​ፋ​ልና።


እኔም ባሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚ​ህች ክፉ ትው​ልድ የተ​ረፉ ቅሬ​ቶች ሁሉ፥ ከሕ​ይ​ወት ይልቅ ሞትን ይመ​ር​ጣሉ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “ፈጽ​መህ ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው።


ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።


እን​ዲ​ህስ ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ፥ በፊ​ትህ ይቅ​ር​ታን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ፥ እባ​ክህ፥ ፈጽሞ ግደ​ለኝ።”


ሙሴ​ንም ተጣ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞ​ትን ኖሮ፤


እኔ ግን ይህ​ንም ቢሆን አል​ፈ​ቀ​ድ​ሁ​ትም፤ ይህን የጻ​ፍ​ሁም ይህን እን​ዳ​ገኝ ብዬ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ምስ​ጋ​ናዬ ከሚ​ቀ​ር​ብኝ ሞት ይሻ​ለ​ኛል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos