ሽማግሎች ይደነግጣሉ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ይይዛቸዋል፤ እርስ በርሳቸውም ይገዳደላሉ፤ ይደነቃሉ፤ ፊታቸውም እንደ እሳት ይንበለበላል።
ኤርምያስ 48:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐቄርዮት ተያዘች፤ አንባዎችዋም ተወስደዋል፤ በዚያም ቀን የሞአብ ኀያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተሞቹ ይወረራሉ፤ ምሽጎቹም ይያዛሉ፤ በዚያ ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ሆኖአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተሞችና ምሽጎች ሁሉ ይያዛሉ፤ በዚያን ጊዜ የሞአብ ወታደሮች በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ሆነው በፍርሃት ይጨነቃሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል። |
ሽማግሎች ይደነግጣሉ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ይይዛቸዋል፤ እርስ በርሳቸውም ይገዳደላሉ፤ ይደነቃሉ፤ ፊታቸውም እንደ እሳት ይንበለበላል።
ስለዚህም ወገቤ ሕማም ተሞላ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ያዘኝ፤ ከሕማሜ የተነሣ አልሰማም፤ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።
ጠይቁ፤ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍረት ተለውጦ አየሁ?
እንደምታምጥ፥ የበኵር ልጅዋንም እንደምትወልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸትሽን ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ሰለለ፤ እጆችዋንም ትዘረጋለች፤ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።
በዚያም ቀን ይላል እግዚአብሔር፤ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፤ ካህናቱም ይደነግጣሉ፤ ነቢያቱም ያደንቃሉ።
እነሆ እንደ ንስር ወጥቶ ይመለከታል፤ ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኀያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።
ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ፥ በመካከልዋም በተቀላቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በመዝገቦችዋ ላይ አለ፤ ይበተናሉም።
የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የከተሞችዋንም መሠረቶች ትበላለች፤ ሞዓብም በድካምና በውካታ፥ በመለከትም ድምፅ ይሞታል፤