በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
ኤርምያስ 28:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳንም ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ ሌሎች ከይሁዳ ወደ ባቢሎን ተማርከው የተወሰዱትንም ሁሉ ወደዚህ ስፍራ እመልሳለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ የጫነባቸውን ቀንበር እሰብራለሁና።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና፥ የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚህች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና፥ ይላል ጌታ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የኢዮአቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ወደ ባቢሎን ተሰደው ከሄዱት ከይሁዳ ሕዝብ ጋር መልሼ አመጣዋለሁ፤ አዎ! የባቢሎንን ንጉሥ የአገዛዝ ቀንበር እሰብራለሁ፤’ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚህች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፥ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና። |
በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
ኢየሩሳሌምንም አጠፋት፥ አለቆቹንም ሁሉ፥ ጽኑዓኑንና ኀያላኑን ሁሉ፥ ጠራቢዎቹንም ሁሉ፥ ብረት ሠራተኞቹንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምርኮኞችን ሁሉ አፈለሰ፤ ከሀገሩ ድሆች በቀር ማንም አልቀረም።
በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ በላያቸው የነበረው ቀንበር ተነሥቶአልና፥ በጫንቃቸው የነበረውንም፥ የአስጨናቂዎችንም በትር መልሶአልና።
ከጥንት ጀምሬ ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ፤ እስራትሽንም ቈርጫለሁ፤ አንቺም፦ አላገለግልም አልሽ፤ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፤ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፥ የተወለደባትንም ሀገር አያይምና ለሚወጣ እጅግ አልቅሱ እንጂ ለሞተ አታልቅሱ፤ አትዘኑለትም።
“እኔ ሕያው ነኝ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን ሆይ፥ አንተን በሰወርሁበት ቀኝ እጄ እንዳለ ማሕተም ነበርህ፤ እንግዲህ ወዲህ ግን እንደማትኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግዚአብሔር፤
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች፥ ብልሃተኞችንና እስረኞችን፥ ጓደኞቻቸውንም ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ከአፈለሳቸው በኋላ፥ እነሆ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ቅርጫቶችን አሳየኝ።
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለበጎነት እመለከተዋለሁ።
“ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከንደነፆር የማይገዛውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ነቢዩ ኤርምያስ ወደ ተረፉት የምርኮ ሽማግሌዎች፥ ወደ ካህናቱም፥ ወደ ሐሰተኞች ነቢያቱም፥ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃል ይህ ነው።
ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያንና እቴጌዪቱ፥ ጃንደረቦቹም፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች ነጻዎችና እሥረኞች፥ ብልሃተኞችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፤ እስራትህንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለሌላ አትገዛም።
ባሪያዎች ከነበራችሁበት ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ በግልጽም አወጣኋችሁ።