Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 29:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ወደ ተረ​ፉት የም​ርኮ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ወደ ካህ​ና​ቱም፥ ወደ ሐሰ​ተ​ኞች ነቢ​ያ​ቱም፥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ማርኮ ወዳ​ፈ​ለ​ሰ​ውም ሕዝብ ሁሉ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የላ​ከው የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ነቢዩ ኤርምያስ በምርኮ ተወስደው በሕይወት ለቀሩት ሽማግሌዎች፣ ለካህናቱ፣ ለነቢያቱና ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ለወሰዳቸው ሕዝብ ሁሉ የላከው የደብዳቤ ቃል ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ነቢዩ ኤርምያስ ተማርከው ወደ ተረፉት ሽማግሌዎች፥ ወደ ካህናቱም፥ ወደ ነቢያቱም፥ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃላት ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ለወሰዳቸው ካህናትና ነቢያት ለሕዝብ አለቆችና ለሌሎችም ስደተኞች ሁሉ ከኢየሩሳሌም የጻፍኩት ደብዳቤ ይዘት እንዲህ የሚል ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ነቢዩ ኤርምያስ ወደ ተረፉት የምርኮ ሽማግሌዎች፥ ወደ ካህናቱም፥ ወደ ነቢያቱም፥ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 29:1
16 Referencias Cruzadas  

ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የም​ክ​ርን ቃል እን​ድ​ት​ቀ​በሉ እመ​ክ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጥ​ቂት ቃል ጽፌ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


እን​ዲህ የም​ትል መል​እ​ክ​ትም በእ​ጃ​ቸው ጻፉ፤ “ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትና ከቀ​ሳ​ው​ስት ከወ​ን​ድ​ሞ​ችም በአ​ን​ጾ​ኪያ፥ በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅያ ለሚ​ኖሩ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ላመኑ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ትድ​ረስ፤ ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


መጀ​መ​ሪያ በጻ​ፍ​ሁት መል​እ​ክት ባሳ​ዝ​ና​ች​ሁም እንኳ አያ​ጸ​ጽ​ተ​ኝም፤ ብጸ​ጸ​ትም፥ እነሆ ያች መል​እ​ክት ለጥ​ቂት ጊዜ ብቻ እን​ዳ​ሳ​ዘ​ነ​ቻ​ችሁ አያ​ለሁ።


ወደ ባቢ​ሎ​ንም የሄ​ዱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና የይ​ሁ​ዳን ምርኮ ሁሉ ወደ​ዚች ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ቀን​በር እሰ​ብ​ራ​ለ​ሁና።”


በእጄ እንደ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ እዩ።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ዮአ​ኪን ከእ​ናቱ፥ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ ከአ​ለ​ቆ​ቹም፥ ከጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹም ጋር ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በነ​ገሠ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ያዘው።


ዓመ​ቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ልኮ ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ደው፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ ከእ​ርሱ ጋር አስ​ወ​ሰደ፤ የአ​ባ​ቱን የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ወን​ድም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አነ​ገሠ።


ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ ሐና​ን​ያም በዚ​ያው ዓመት በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ሞተ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ያሉት የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ቻ​ችሁ አያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፤ ሕልም አላ​ሚ​ዎች አለ​ም​ን​ላ​ችሁ የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን አት​ስሙ፥


ስለ​ዚህ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን የሰ​ደ​ድ​ኋ​ችሁ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”


ኤር​ም​ያ​ስም ሠራ​ያን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ባቢ​ሎን በገ​ባህ ጊዜ እይ፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ አን​ብ​ብና፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios