ኤርምያስ 27:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ምድርን ሁሉ ለባሪያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ ያገለግሉትም ዘንድ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እነዚህን አገሮች ሁሉ ለአገልጋዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣለሁ፤ የዱር አራዊት እንኳ እንዲገዙለት አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባርያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ እንዲያገለግሉትም የምድረ በዳን አራዊት ደግሞ ሰጥቼዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሕዝቦች ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ በሆነው በአገልጋዬ በናቡከደነፆር ሥልጣን ሥር እንዲገዙለት ያደረግኹ እኔ ነኝ፤ የምድር አራዊትም ሳይቀሩ ይገዙለታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባሪያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፥ ይገዙለትም ዘንድ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ። |
“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ እርሱም በይሁዳ ባለችው በኢየሩሳሌም ቤትን እሠራለት ዘንድ አዝዞኛል፤ ከሕዝቡም ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም ይውጣ።”
ቂሮስንም፥ “ብልህ ሁን፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስንም እመሠርታለሁ ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” ይላል።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና አገልጋዮቹን፥ ከቸነፈርና ከሰይፍ፥ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትን ሕዝቡንም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፥ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፤ አይራራላቸውም፤ አይምራቸውም።”
ነፍስህንም ለሚሹአት፥ ከፊታቸውም የተነሣ ለምትፈራቸው እጅ፥ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ለከለዳውያንም እጅ እሰጥሃለሁ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች፥ ብልሃተኞችንና እስረኞችን፥ ጓደኞቻቸውንም ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ከአፈለሳቸው በኋላ፥ እነሆ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ቅርጫቶችን አሳየኝ።
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለት ዘንድ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ፤ እነርሱም ይገዙለታል፤ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።”
እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፤ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፤ ጋሻዎቹንም በእነርሱ ላይ ያነሣል።
እናንተ በአሦር የምትኖሩ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፥ ክፉ አሳብንም አስቦባችኋልና ሽሹ፤ ወደ ሩቅም ሂዱ፤ በጥልቅ ጕድጓድም ውስጥ ተቀመጡ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ባድማም በሆኑ ምድሮች መካከል የግብፅን ምድር ባድማ አደርጋታለሁ፤ በፈረሱትም ከተሞች መካከል ከተሞችዋ አርባ ዓመት ፈርሰው ይቀመጣሉ፤ ግብፃውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናቸዋለሁ፤ በሀገሮችም እዘራቸዋለሁ።”
የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ፤ ግብፅንም ይወጋበታል፥ ምርኮዋንም ይማርካል፤ ሰለባዋንም ይሰልባል።