ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፥ “እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጣለች” አለው።
ኤርምያስ 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለራሴ ሰፊ ቤት፥ ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፥ መስኮትንም ለሚያወጣ፥ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጥ፥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ባለትልልቅ ሰገነት፣ ሰፊ ቤተ መንግሥት ለራሴ እሠራለሁ’ ለሚል ወዮለት! ሰፋፊ መስኮቶችን ያበጅለታል፤ በዝግባ ዕንጨት ያስጌጠዋል፤ ቀይ ቀለምም ይቀባዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ’ ለሚል፥ መስኮቶችንም ለሚያወጣለት፥ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጠው፥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሰው “ለራሴ ትልቅ ቤት ከሰፊ ሰገነት ጋር እሠራለሁ፤ እንዲሁም ሰፋፊ መስኮቶችን አወጣለታለሁ፤ ቤቱን በሰፋፊ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስጌጠዋለሁ፤ ደማቅ ቀይ ቀለምም እቀባዋለሁ” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፥ መስኮትንም ለሚያወጣ፥ በዝግባም ሥራ ለሚያሳጌጥ፥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት! |
ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፥ “እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጣለች” አለው።
ጌታ እግዚአብሔር፥ “የያዕቆብን ትዕቢት አረክሳለሁ፤ ሀገሮቹንም ጠላሁ፤ ከተሞቹንም ከሚኖሩባቸው ሰዎች ጋር አጠፋለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአልና።
ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፣ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።