የግብፅም ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ የይሁዳን ንጉሥ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ ፋንታ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠ፤ ፈርዖን ኒካዑም ወንድሙን ኢዮአክስን ይዞ ወደ ግብፅ ወሰደው። በዚያም ሞተ። 4 ‘ሀ’ ወርቅንና ብርን ለፈርዖን ሰጠ። በዚያን ጊዜም ምድር በፈርዖን ትእዛዝ ብር መገበሯን ጀመረች። 4 ‘ለ’ እያንዳንዱም እንደሚችለው ለፈርዖን ኒካዑ እንዲገብር ከሀገሪቱ ሕዝብ ወርቅንና ብርን ጠየቀ።