ኤርምያስ 22:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በአባትህ ዝግባ አዳራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ አይበላና አይጠጣም ነበርን? ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 “በዝግባ ዕንጨት ብዛት፣ የነገሥህ ይመስልሃልን? አባትህስ ፍትሕንና ጽድቅን በማድረጉ፣ የሚበላውና የሚጠጣው ጐድሎት ነበርን? እነሆ፤ ሁሉም መልካም ሆነለት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ ይበላና ይጠጣ ፍርድንና ጽድቅን ያደርግ አልነበረምን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ሌሎች ሰዎች ከሚያደርጉት ይበልጥ ምርጥ በሆነ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቤትህን በመሥራትህ የተሻልክ ንጉሥ የሆንክ ይመስልሃልን? አባትህ ደስታ የሞላበት ሙሉ ዕድሜ ነበረው፤ እርሱ ዘወትር ትክክለኛና ቅን ከመሆኑ የተነሣ የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ አይበላምና አይጠጣም ነበርን? ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። Ver Capítulo |